Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማ  ዘማቾች ዛሬ  አሸኛኘት  ተደረገላቸዉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የጎንደር ከተማ  ዘማቾች ዛሬ  አሸኛኘት  እንደተደረገላቸው የከተማ አስተዳደሩ  አስታወቀ።

በአሸኛኘት ስነ ስርዓቱ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ፥ ትህነግ ሀብታችን ዘርፏል ፣ የሀይማኖት ተቋማትን አቃጥሏል፣ሴቶችን ደፍሯል ብለዋል።
“የምንዋጋዉ ለፍትህና ለነጻነት ነዉ፡፡ጀግናዉ የአማራ ህዝብ የተቃጣበትን ጦርነት በድል እንደሚያጠናቅቀዉ እተማመናለሁ” ብለዋል።
የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘዉዱ ማለደ በበኩላቸው፥ የተቃጣብን ወረራ ለመመከት ያጋጠመው የአመራርና የአደረጃጀት ክፍተቶች የተሟሉ መሆኑን ገልጸዉ፥በሁሉም ግንባር ዘመቻዉ በድል ይጠናቀቃል ብለዋል።
ዘማቾችም በዚህ ታሪካዊ ጦርነት በመሳተፋቸዉ ደስታቸዉን መግለጻቸውን ከጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.