Fana: At a Speed of Life!

“ትዳሬ እና ልጆቼ ከሀገሬ አይበልጡም”

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክተት ጥሪ ተቀብለው ለመዝመት የተመዘገቡ ሚሊሻ አባል የሽብርተኛውን ትህነግ ወራሪ ቡድን ለመደምሰስ ከአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የተላለፈውን የክተት ጥሪ ተከትሎ በርካቶች ፈጣን ምላሽ በመስጠት ወደ ግንባር መትመማቸዉን ቀጥለዋል፡፡

አቶ ወተቱ አሰፋ  እና  አቶ ሙሉጌታ ወርቅነህ ም በሃገሬ ለመጣ ለአፍታም አንታገስም  በማለት  የክተት ጥሪውን  የተቀበሉ  የባህር ዳር ነዋሪዎች ናቸው፡፡

አቶ ወተቱ አሰፋ  የግሽዓባይ ክፍለ ከተማ  ነዋሪ ሲሆኑ÷  ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባትም ናቸው ፤የሚሊሻ ስልጠና ወስደው ክፍለ ከተማውን እያገለገሉ  ኑሯቸውን ይገፉ እንደነበር  ይናገራሉ ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ምንም እንኳን  የቤተሰብ ሃላፊነት ቢኖርባቸዉም  ሁሉም ነገር በሀገር ነውና ሃገሬን በዚህ ሁኔታ እያለች እጅን አጣጥፌ አልቀመጥም በማለት  በክተት ጥሪው ለመሳተፍ  ዝግጁ ሆነዋል ፡፡

አቶ ወተቱ እንዳሉት ሽብርተኛው  ወራሪ ቡድን በአማራ እና በአፋር ክልሎች ዘር የማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ ነው፤ይህ ጭካኔ በየደጃችን እንዳይደርስ ልናስቆመው ይገባል ይላሉ፡፡

ይህንን ሽብርተኛ ቡድን ለማስቆም ሁሉም የድርሻዉን መወጣት ስላለበት  እኔም ትዳሬ እና ልጆቼ ከሀገሬ አይበልጡም በማለት የክተት ጥሪውን በመቀበል ሀገርን ለማዳን ለሚደረገው  ዘመቻ ያላቸዉን  ቁርጠኝነት  ይገልጻሉ፡፡

አማራን ብሎም ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተነሳውን የሽብርተኛ  ቡድን ለመደምሰስ ዛሬ ነገ አያስፈልገውም  ያሉት አቶ ወተቱ ÷ እንደ ግሽዓባይ ክፍለ ከተማ ሁሉም የመንግሥትም ሆነ የግል ታጣቂ በየአደረጃጀቱ እየተዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ ወጣቶች ሀገራቸውን ለማዳን መሰለፍ አለባቸዉ ያሉት ደግሞ  በባሕር ዳር ከተማ አስተዳዳር ግሽዓባይ ክፍለ ከተማ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት የሻለቃ መሪ  የሆኑትአቶ ሙሉጌታ ወርቅነህ  ናቸው፡፡

ቤተሰቦቻቸውን በንግድ ሥራ  የሚያስተዳድሩት አቶ ሙሉጌታ ÷ ሽብርተኛው ቡድን እያደረሰ ያለውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ለማስቆም የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ ተቀብለው ወደ ግንባር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡

እንደ አቶ ሙሉጌታ  ሽብርተኛው ቡድን አማራን በማጥፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳ ነው፤ ይህን ሽብርተኛ ቡድን ለመደምሰስ ደግሞ ሁሉም ወደ ግንባር መዝመት እንዳለበት ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡

አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው እና አጥንታቸውን ከስክሰው ያቆዩአትን ሀገር ለወራሪ አሳልፎ ላለመስጠት ሁሉም መስዋዕትነት መክፈል አለበት፤ ለዚህም መዘጋጀት ተገቢ ነው ይላሉ፡፡

የሀገራችን እጣ ፈንታ የሚወሰነው በወጣቱ ላይ በመሆኑ   ወጣቱ ጉልበቱን፤ እውቀቱን እና ብልሃቱን ተጠቅሞ ሃገሩን ከመፍረስ ለማዳን  ሊጠቀምበት ይገባል ነው ያሉት፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

 

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

 

መከላከያን ይደግፉ!

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.