Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ በትክክለኛ ወቅት እየተገነባ ያለ ግድብ ነው -የዩጋንዳ ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በትክክለኛ ወቅት እየተገነባ ያለ ግድብ እና የአፍሪካ ህብረትም የድርድሩ ትክክለኛ መድረክ ነው ሲሉ የዩጋንዳ ምሁራን ገለጹ።
የዩጋንዳ የውጭ ግንኙነት ምክር ቤት ባዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ የተሳተፉ ተመራማሪዎች እና አጥኝዎች የአባይ ወንዝ ብዙ አገራት የሚጋሩት እና እንደ ህዝብም የሚያስተሳስራቸው ታላቁ የአህጉሩ ወንዝ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ወንዝ ላይ እየገነባች ያለውን ግድብ በማጠናቀቅ ላይ ስትሆን ግድቡም 6 ሺህ ሜጋ ዋት በማመንጨት ለቀጠናው የኤሌክትሪክ ሃይል እንዲዳረስ እየሰራች ነው መሆኑንም ጠቁመዋል።
በአውደ ጥናቱ የተለያዩ ምሁራን ጽሁፎች ያቀረቡ ሲሆን በበይነ መረብ ውይይት ተካሄዷል።
በእለቱም በምስራቅ አፍሪካ ግጭት ላይ በምርምር ስራቸው የሚታወቁት የመካራሪ ዩኒቨርሲቲ መምህር ፕሮፌሰር ካሳጃ ፒሊፕ ጥናት አቅርበዋል።
የፅሁፉ አቅራቢ የአፍሪካ ህብረት ድርድሩን ለመምራት መዋቅራዊ አደረጃጀት ያለው፣ ህጋዊ እና ለዚህ ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም መሆኑን አንስተዋል።
ሶስቱ አገራት የህብረቱ አባል አገራት በመሆናቸው ይህ ጉዳይ የሚታይበት ትክክለኛ ቦታ ነው በማለት አስረድተዋል።
በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለምፀሐይ መሰረት ፥ መድረኩን ያዘጋጀው የዩጋንዳ የውጭ የዉጭ ግንኙነት ምክር ቤትን አመስግነዋል።
አፍሪካውያን እውነቱን በመረዳት ሶስቱ አገራት ለሁሉም በሚጠቅም መልኩ ውጤት ላይ እንዲደርሱ ድጋፍ ማድረግ አለባቸው መባሉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.