Fana: At a Speed of Life!

ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኝ የጦር መሳሪያ  በ11ዱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ተቋማት  ማስመዝገብ አለበት -የአዲስ አበባ ፖሊስ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኝ የጦር መሳሪያ በሁለት ቀናት ውስጥ በ11 ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በስራ ሰዓት በግንባር ቀርቦ ማስመዝገብ እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ በጋራ በመሆን አካባቢውን ሲጠብቅ ጥበቃውን የተጠናከረ ማድረግ እንዲረዳው  ማንኛውም  ሰው በእጁ የሚገኝ  የጦር መሳሪያ በሁለት ቀናት ጊዜ ውስጥ በአስራ አንዱም  ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር በመቅረብ እንዲያስመዘግብ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የመዲናዋ ፖሊስ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከርና መረጃ በመለዋወጥ አካባቢውን ከፀረ-ሰላም ሃይሎች መጠበቅ እንዲችል ምዝገባው ማስፈለጉን ተገንዝቦ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማንኛውም  ግለሰብ በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ በማስመዝገብ ህጋዊነቱን ተላብሶ የጦር መሳሪያውን ተጠቅሞ እራሱን እና አካባቢውን  እንዲጠብቅበት መልዕክቱን ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.