Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ጉዟችን በጁንታው መሰሪ ተንኮልና ተላላኪዎች አይደናቀፍም -አቶ ከድር ጁሀር

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ጉዟችን በጁንታው መሰሪ ተንኮልና ተላላኪዎች አይደናቀፍም ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ገለፁ፡፡

ከንቲባው ኢትዮጵያ በከሀዲው ጁንታ እየተወጋች ነው ፤በጁንታው አዛውንት ፣ ሴቶች ፣ ህጻናት ፣ ወጠቶች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ ብቻ አሰቃቂ ሞት ተፈጽሞባቸዋል ብለዋል ፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ ከተሞች አንበጣ የማሽላ ማሳን እንደሚያወድም ጁንታውም ትምህርት ቤቶችን ፣ የህክምና መዕከላትን ፣ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን ፣ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ፣ ባንኮችን እና የአገልግሎት ተቋማትን የቻለውን ሁሉ እየዘረፈ ያልቻለውን በእሳት እያቃጠለ ይገኛል ፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የጸጥታ ኃይል በዓለም አቀፍ የጦርነት ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ገድል የፈጸመና ሀገርን የታደገ ጠንካራ መከታችን ነው ፡፡

በዓለም አደባባይ ዜጎች እንኳንም ከኢትዮጵያ ተፈጠርን ብለው አንገታቸውን ቀና አድረገው እንዲሄዱ ያስቻለ ድንቅ ሰራዊት ነው ያለን ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር መከላከያ ኃይላችንና የጸጥታ ኃይሉ እየከፈሉ ላሉት መስዋትነትና ለሚፈጸሙት ታሪክ ታላቅ ክብር አለው ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደርና የድሬዳዋ ህዝብ በቀጣይ ለሚደረገው የህልውና ጦርነት ከሀገር መከላከያ ራዊት ጎን በመሰለፍ ጦርነቱ በአጭር ጊዜ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና እንድትወጣ የምንሰስተው ሀብት ፣ የምናከመቸው ቁስ አይኖረንም ብለዋል ፡፡

በጦርነቱ ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ መጠለያ ጣብያዎች የሚገኙ ወገኖቻችንን የማቋቋም ግዙፍ ስራ የድሬዳዋ አስተዳደርና ህዝብ ዋንኛ ቁልፍ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር አመራር ለሀገር ህልውና የሀገራዊ የክተት ዘመቻ ጥሪን ተከትሎ ወቅቱ የሚጠይቀውን ማንኛውንም ሀገራዊ ኃላፊነት ህዝባችንን በማሰለፍ እና በማስተባበር አውደ ውጊያው ድረስ በመዝመት እስከ ህይወት መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጣለው ብለዋል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር የምትገኙ ወጣቶችም የነገ ተሰፋችሁን ለማጨለም ጁንታው በኢትዮጵያ ላይ የህልውና አደጋ ጋርዷል ፤ ወጣቱ ከአባቱና ከአያቱ የተረከባትን ሀገር እሱም በተራው ከነጻነቷና የግዛት አንድነቷ ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ ታላቅ ኃላፊነት በትከሻው ላይ ወድቋል ነው ያሉት ከንቲባው ፡፡

በመሆኑም ከመንግስት የቀረበልህን የህልውና ዘመቻ የክተት ጥሪ በመቀበል የህይወት መስዋትነት ጭምር በመክፈል ሀገርን እንድትታደግ ጥሪ እናቀርባለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ቀሪው የድሬዳዋ ህዝብም ከሀገር መከላከያ ፣ ከፌደራል ፖሊስ ፣ ከድሬዳዋ ፖሊስና ልዩ ኃይል ጋር በመናበብ ጸጉረ ልውጦች ሲመጡ በማሳወቅ አካባቢህን ነቅተህ መጠበቅ ወቅቱ የሚጠይቀው የዜግነት ግዴታ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.