Fana: At a Speed of Life!

ለከዳዉ ቡድን ዋጋዉን ለመክፈል ሁሉም በሙሉ ወኔ ተዘጋጅቷል-የዞን አስተዳዳሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለከዳዉ ቡድን ዋጋዉን ለመክፈል ሁሉም በሙሉ ወኔ ተዘጋጅቷል ሲሉ የደቡብ ጎንደር እና የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪዎች ተናገሩ።
ህዝብን ከጥፋት ሀገርንም ከመፍረስ ለማዳን የተደረገው ጥሪ በተግባር እየተተረጎመ መሆኑን የሚገልፁት የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ ሲሳይ ቅጣዉ ÷ የክተት ጥሪውም እንደ ክልልም ይሁን እንደ ሀገር ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመቋጨት ያለው አማራጭ ነዉ ብለዋል፡፡
ድልና ማሸነፍ የሚገኘዉ በመስዋትነት በመሆኑ የደቡብ ጎንደር ህዝብ ይህን ለማድረግ ሁሉንም አስፈላጊ ተግባራት እየፈፀመ ነዉ ብለዋል።
አቶ ይርጋ የክተት ምላሹ ጠላትን በሚገባ ከማዳከም ባለፈ ባለበት እንዲከስምና የሚያደርሳቸዉን እኩይ ተግባራት ለማምከን ያስችላል ነው ያሉት።
ስለሆነም ሁሉም የዞኑና የክልል ነዎሪዎች ያላቸዉን ሁሉንም አይነት መሳሪያ በመጠቀም ወገኖቻችንን ከሞት ሀገራችንን ከመፍረስ እንታደግ ሲሉም አሳስበዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደሪ አቶ ታደሰ ገብረ ፃዲቅ ÷ይህን ወራሪ ሀይል ባለበት ለመቅበርና ለከዳዉ ቡድን ዋጋዉን ለመክፈል ሁሉም በሙሉ ወኔ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
የቀደሙ አያቶቻቸንን እና እናት አባቶቻችን አደራን ለመወጣት የዞኑ ነዋሪ ከሚገመተዉና ከሚታሰበዉ በላይ ጠላቱን ላይመለስ ለመሸኘት አስፈላጊዉ ሁሉ ተጠናቋል ብለዋል።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የዞን አመራሮቹ ÷ወራሪዉ ሀይል እያደረሰዉ ያለዉን ጉዳት ለመመከት ቁርጠኛ እንደሆኑ አረጋገጠዋል።
አመራሩም የህዝብን፣ የሀገርና ወገንን የመታደግ ተግባርን በግንባር ቀደምትነት እንደሚወጣና ማህበረሰቡ በማያዉቀዉ ጓዳ ጎድጓዳ ሁሉ በመግባት ጠላትን መደምሰስ እንደሚገባዉም አመራሮቹ አሳስበዋል።
በመሃመድ አሊ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
No photo description available.
0
People reached
250
Engagements
Distribution Score
Boost Post
232
10 Comments
8 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.