Fana: At a Speed of Life!

የሽብር ቡድኑን ለማስወገድ የጀመርነው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን ዳግም ወደ ስልጣን ለመመለስ የሚያደርገው መፍጨርጨር ተራ ልፋት ሆኖ ይቀራል ብለዋል የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት አስተያየት ሰጪዎቹ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን በግፍ የተሞሉ ጊዜያት ውስጥ ማለፍ የሽብር ቡድኑ ድርጊቶች ምክንያት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ቡድኑ በክልላቸው ለዘመናት ተጋብተው እና ተዋልደው አብሮ ይኖሩ የነበሩ ብሄር ብሄረሰቦች በሰላም እንዳይኖሩም ትልቅ ሚና ነበረው ብለዋል።

ከለውጥ በፊት በነበሩት ጊዜያትም ቁልፍ የክልሉ ስልጣንን እየተቆጣጠረ የክልሉን ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ነፍጎ መቆየቱንም ነው ያነሱት።

በጉልበት፣ ገንዘብ እና ሞራል ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሠለፍ ቡድኑን ለማስወገድ የጀመሩትን ስራ እንደሚቀጥሉም አንስተዋል።

አፈወርቅ አለሙ እና ፈቲያ አብደላ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.