Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ነው፡፡
በሰሜን እዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ የምክር ቤት አባላቱ የህሊና ፀሎት አድርገዋል፡፡
አስተያታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ የምክር ቤት አባላት እንደገለጹት÷ ህወሓት በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የፈፀመው አስነዋሪ ተግባር አሳፋሪ በመሆኑ÷ አሸባሪው ቡድን በንፁሃን ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃትም በጋራ በመቆም መታል እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
ሀገርን ለማፍረስ የተነሳውን የጁንታውን ቡድን ስልጣን የመያዝ ጥማቱንና አረመኔያዊ ተግባሩን ተባብሮ በመታገል በአጭር ጊዜ እንዲቋጭ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ምክር ቤቱም በዛሬ ውሎው÷ የ6ኛው ዙር ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ረቂቅ ቃለ ጉባኤን መርምሮ ማፅደቅ ከዚያም በቀረበው ሞሽን ላይ ተወያይቶ ያፅድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመሆን ጥያቄን ሂደት የሚያመላክት ሪፖርትና የስልጣን ርክክብ እንደሚኖር በመርሃ ግብሩ ላይ ተመላክቷል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.