Fana: At a Speed of Life!

በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አንረሳውም – የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን አስከፊ ጭፍጨፋ እና ክህደት መቼም አንረሳውም ሲል የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ጥቅምት 24/2014 ህወሓት በሀገር መከላያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ጭፍጨፋ አስመልቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
መቼም ቢሆን፣ የትም ቢሆን፣ በምንምም ቢሆን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የሆነውን አንረሳውም፤ በፍፁም!!
አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሆን ብሎ በቀየሰው የጥፋት ሴራ፣ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ከ20 ዓመታት በላይ የትግራይ ህዝብን ከጠላት ሲጠብቅ የነበረ፣ ለተቸገሩ ተጋሩ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ ሲያግዝ የነበረ፣ ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያና መንገድ የሌሉበት መንደሮች፣ በገንዘቡ እና በጉልበቱ ሰርቶና አሰርቶ፤ የትግራይ ህፃናት እንዲማሩ፣ የታመሙ በአቅራቢያቸው እንዲታከሙ እና መንደሮች እንዲገናኙ ሲያደርግ ኖሯል።
የሽማግሌዎች እና ዓቅመ ደካማ አርሶ አደሮች ምርታቸውን በአንበጣ መንጋ እንዳወድም ቀን ከሌሊት ሲደክም የነበረ፣ የተዋለደ፣ የተዛመደና የተጋመደ፣ ፅኑ መሰረት የነበረው የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊታችን፣ ከትግራይ ህዝብ ጋር ሲለፋና ሲደክም ውሎ፣ “አገር አማን” ብሎ በተኛበት፣ በአሸበሪው ቡድን የተፈፀመበት አሰቃቂ ክህደት የተሞላበት የግፍ ሰቃይ መቼም ቢሆን፣ የትም ቢሆን፣ በምንምም ቢሆን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም አንረሳትም።
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን ሉአላዊነት የተደፈረባት፣ ተጋሩን በማይወክል የሌቦችና ከሃዲዎች ስብስብ በፈፀመው እና ባስፈፀመው አሰቃቂ ድርጊት የንፁሃን ተጋሩ በኢትዮጵያውነታቸው እንዲጠረጠሩ ያደረገች ጥቁር ቀን ናት።
ጥቅም 24 ቀን 2013 ዓ.ም ንፁሃን ተጋሩ ለችግር እንዲጋለጡ፣ ኢትዮጵያውያን ውድ ህይወታቸው እና ዋጋ እንዲከፍሉ ያደረገች፣ የአገር ሉአላዊነት የተደፈረባት ቀን ናት።
“ያለፈን ስህተት የማይደግም አመራርም ሆነ ህዝብ አስተዋይ ነው”! አሁንም የኢትዮጵያን ጠላት፣ የምዕተ ዓመት ሸክም አሸባሪው ህወሓት ነው።
ስለሆነም ይህ ‘አገር ለማፍረስ ሲኦልም ቢሆን እገባለሁ’ ብሎ የትግራይን ህዝብ እንደ ዕቁብ ቀብድ አሲዞ በንፁሃን ኢትዮጵያውያን በተለይ ደግሞ በአማራ እና በዓፋር ወንድም እና እህት ህዝቦች እያደረሰው ያለው የሰው ፍጅት እና ሞት፣ የእንስሳት መግደል፣ የደን መጨፍጨፍ ከማንም በላይ በቅድሚያ ተጋሩ ልንኮንነው፣ ልንቃወመው፣ ልናወግዘው ይገባል።
በተለይ በአዲስ አበባ ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ያላቹ ተጋሩ ከውሸት የአሸባሪውን ህወሓት የሙት ፕሮፖጋንዳ እና ቅዠት ርቃቹ ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከኢትዮጵያ መከላካያ ሰራዊታችን ጎን እንድትሰለፉ እና ኢትዮጵያዊነታቹን እንድታስመሰክሩ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ታሸንፋለች!!
ክብር ኢትዮጵያን ሲሉ ለተሰዉ ወገኖቻችን!!
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.