Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የፈጸመበት አንደኛ ዓመት በክልሎች ታስቦ ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት የሰነዘረበት አንደኛ ዓመት በተለያዩ ክልሎች ታስቦ ውሏል፡፡

በሃረሪ ክልል በተደረገው የመታሰቢያ ስነስርዓት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኦድሪን በድሪን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቀኑን አስበው ውለዋል።

የእናት ጡት ነካሹ ህወሓት እንደ ቀበሮ በጉድጓድ ሆኖ ሲጠብቀው በነበረው ሰራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት በዓለም ታሪክ ተሰምቶ እንደማያውቅ እድምተኞቹ ተናግረዋል።

ጁንታው አሁን ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ጥቃት ከመመከት አንፃርም የክልላቸውን ሠላም ከማስጠበቅ ጀምሮ ግንባር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ የሠነዘረው ጥቃትና ከዚያም በኋላ በአፋርና አማራ ክልሎች ያደረሰው ጭፍጨፋ ከኢትዮጵያዊነት ስነምግባር የራቀና የቡድኑን አረመኔያዊነት ያንፀባረቀ ነው ብለዋል።

በሻማ ማብራት ታስቦ የዋለው ቀኑ ÷ ለእናት ሀገር በክብር እየተዋደቀ ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ደም የተለገሰበትም ሆኗል።

በተጨማሪም ቀኑ በጋምቤላ ክልል እየታሰበ የሚገኝ ሲሆን ÷ መርሃ ግብሩ ‹‹አልረሳውም እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ›› በሚል መሪ ቃል በአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት እና በጧፍ ማብራት ስነ ስርዓት ነው የተከበረው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ርዕሠ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው እንዳሉት ÷ ለሀገር ሰላም ለወገን የተረጋጋ ህይወት ውድ ህይወቱን ለመገበር ሳይሳሳ የተሰለፈውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሀገር ሻጩ እና ባንዳው ወያኔ ከጀርባ የወጋበት ቀን ነው፡፡

ወቅቱ እንደ ሃገር የገጠመንን ፈተና ለመሻገር ሁላችንም በአንድነት በፅናት የምንቆምበት እንደሆነ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ትግሉ ዋጋ ማስከፈሉ ባይቀርም የመጨረሻዋን ድል እንደምንቀዳጅ ጥርጥር የለንም ብለዋል።

በተመሳሳይ በደቡብ ክልል ቀኑ በሻማ ማብራት እና በሽብር ቡድኑ ለተሰው ጀግኖች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ስነ ስርዓት በማከሄድ ተስቦ ውሏል፡፡

በፕሮግራሙ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ፣የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ ፣ የደቡብ ክልል ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የክልሉ ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም፤ ተጨማሪ መረጃ ከክልሎች መንግስት ኮሙዩኒኬሽን

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.