Fana: At a Speed of Life!

ጠላትን በደማችን እና በአጥንታችን ቀብረን የኢትዮጵያን ክብር ቀና እናደርጋለን- ጠ/ሚ ዐቢይ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ የክህደት ጥቃትና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ያካሄደበት አንደኛ ዓመት በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየታሰበ ነው።

በመታሰቢያ መርሃ ግበሩ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዕለቱን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ጥቅምት 24 ኢትዮጵያን ብለው ፣ ሰፈራቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ትተው ሀገራቸውን ከጥቃት ህዝባቸውን ከመከራ ሊታደጉ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተሰለፉ ወንድሞቻችን እራሳቸው አብልተው፣ አልብሰው ሰው ያደረጓቸው የሽብር ቡድኑ ህወሓት አባላት በግፍ፣ በጭካኔ ሰውኛ ባልሆነ መንገድ የተጨፈጨፉበት ዕለት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ጥቅምት 24 ቀን በትግራይ በግፍ የተገደሉት ወንድሞቻችን ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያም በዕለቱ ተገድላለች፤ የኢትዮጵያ ህዝቦችም በዕለቱ ተጨፍጭፈዋል ነው ያሉት፡፡

ዕለቱ እኛ ዛሬ በህይወት ያለን እኔም ወታደር ነኝ የምንል የኢትዮጵያ ልጆችም እኩይ ሃሳብ ይዘው ሀገራችን ለማዋረድ፣ ለመበተን፣ ክብራችን ለማውረድ የተነሱትን ሃይሎች ለመቅበር አንድ መሆናችንን እና በእኛ መስዋዕትነት ሀገራችን የምትቀጥል መሆኗን ዳግም ቃል ኪዳን የምንገባበት ነው ብለዋል፡፡

ይህ ወሮበላ የሆነው ስብስብ በየሄደበት እየወረረ ከህዝብ እየቀማ የሚበላ፣ የሚሸጠው ሃሳብ የሌለው ዘራፊ ቡድን አሁንም ይበልጥ ሀገራችንን ለማፍረስ ጉድጓድ እየቆፈረ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ይህ በጥልቀት የሚቆፍረው ጉድጓድ ጠላት የሚቀበርበት እንጂ ኢትዮጵያ የምትፈርስብት አይሆንም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፡፡

ይህን ጠላት በደማችን፣ በአጥንታችን ቀብረን ኢትዮጵያን ቀና እናደርጋለን፣ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማም ከፍ እናደርጋለን ነው ያሉት።

የኢትዮጵያን ዘመን የማይረሳቸው ጠላቶች እናዋርዳለን እንጂ ኢትዮጵያ አትዋረድም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ኢትዮጵያን ዝቅ ለማድረግ ተገዝቶ የራሱ ሃሳብ የሌለው ባንዳ እየፈጸመብን ያለውን በደል እሱን ብቻ ሳይሆን ከጀርባው ሃሳብ ያሸከሙትን ጭምር በኢትዮጵያ አንድነት የምናሸንፍ መሆኑን የምናረጋግጥበት ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ኢትዮጵያ በእኛ መስዋዕትነት የምትቀጥል እንጂ የምትፈርሰ አለመሆኗንም ዳግም ለዓለም ህዝብ የምናረጋግጥበት እድል በእጃችን መሆኑንም አውስተዋል፡፡

ሀገራችን በዘመናት መካከል ሳትሞከር ቀርታ አታውቅም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ÷ ብዙ ሃይሎች ከውስጥ ከውጭም ሲሞክሯት ሊያፈርሷት፣ ሊከፋፍሏት እና ሊያጎሳቁሏትጥረት ሲያደርጉ እንደቆዩ አስታውሰዋል፡፡
በሁሉም መድረክ የኢትዮጵያ ህዝብ ዋስትና አለመሞከር ሳይሆን አንድ ሆኖ ማሸነፍ ነው፤ ተሞክረናል አንድ ሆነን እኛም እንደ አባቶቻችን በመስዋዕትነት ሀገራችን እናስቀጥላለን ጠላቶቻችንም በቆፈሩት ጉድጓድ እንቀብራለንም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡

ኢትዮጵያ ነጸ እስከምትሆን እያንዳንዱ ዜጋ እኔም የኢትዮጵያ ወታደር ነኝ ብሎ የጠላትን ድርጊት በማውገዝ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ጠላትን የሚያሳፍርበት ጊዜው መሆኑንም አስረድተዋል።

እያንዳንዱ ዜጋ የሀገር መከላያ ሰራዊት እየከፈለ ያለውን ዋጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ሰራዊቱን ለማጠናከር በራሱ ፈቃድ እንዲመለመል እና እንዳንዱ ዜጋ ያለውን ትጥቅ ጥይት ለመከላከያ አስፈላጊ በሆነበት ሁሉ በማቅረብ ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው የጋራ ጠላትን በተባበረ ክንድ በቆፈረው ጉድጓድ በመቅበር የኢትዮጵያን ሰላም እና አንድነት ለማረጋገጥ ቃል ኪዳን የሚገባበት ቀን ዛሬ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.