Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የጦር መሳሪያ ያለው ግለሰብ እንዲያስመዘግብ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ማንኛውም የጦር መሳሪያ ያለው ግለሰብ በማስመዝገብ እራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።
የክልሉ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ጥላሁን ዋደራ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ሃላፊው በመግለጫቸው ህዝቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ የጁንታው ሃይል ሀገር ለማፍረስ የያዘውን ህልም ማክሸፍ ይጠበቅበታል ብለዋል።
ይህን ለማድረግ ያስችል ዘንድም በክልሉ የሠላምና ፀጥታ አደረጃጀቶች ከዚህ በፊት ከነበሩት አሰራር በተሻለ መንገድ እንዲሰሩ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።
በትላልቅ ተቋማትና ድርጅቶች የሚደረገው ጥበቃ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ሃላፊው÷ይህንን ለማሳካትም ቋሚና ድንገተኛ ፍተሻዎች በየጊዜው እንደሚካሄድም ነው የገለጹት።
በክልሉ በተለይም በሀረር ከተማ የሚገኙ ቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ሙሉ መረጃ ከመያዝ ባሻገር በአካባቢያቸው ጸጉረ ልውጦችን ሲመለከቱ ለፀጥታ ሃይሎች እንዲጠቁሙ ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ ወጣትም ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ እና የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
 
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.