Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ጦር ኃይሎች አጠቃላይ ሆስፒታል ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ወታደራዊ መደብር እና መዝናኛ ክበቦች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለመከላከያ ጦር ኃይሎች አጠቃላይ ሆስፒታል ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአልባሳት ድጋፍ አደረገ፡፡
ዳይሬክቶሬቱ 1 ሺ 300 ብርድ ልብሶችን ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡
ወታደራዊ መደብር እና መዝናኛ ክበቦች አስተዳደር ሲደራጅ ዋና ዓላማው ሰራዊቱን እና የሰራዊቱ ቤተሰብን ለመደገፍ በመሆኑ÷ ይህንኑ የሚያሳካ ድጋፍ ለራሳችን ቤት ስናደርግ ደስታ ይሰማናል ሲሉ የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ኮ/ል ታደሰ ታምሩ ተናግረዋል፡፡
የጦር ኃይሎች አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና አዛዥ ብ/ጄ ዶ/ር ኃይሉ እንዳሻው ድጋፉ ሆስፒታሉን አንድ ደረጀ ከፍ ያደርገዋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.