Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል ነዋሪዎች ማንኛውንም የነፍሥ ወከፍ መሣሪያ በመያዝ እንዲዘምቱ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ነዋሪ ያለዉን ማናቸዉንም የነፍሥ ወከፍ መሣሪያና ትጥቅ እንዲሁም ተያያዥ ግብዓቶችን በመያዝ ከልዩ ኃይሉና ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን እንዲሠለፍ እና ሕዝቡ ከተደቀነበት አደጋ እንዲታደግ የክልሉ መንግስት ጥሪ አቀረበ።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በመግለጫቸው እንዳሳሰቡት ÷ የክልሉ ሕዝብ ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና ለመበተን የሚንቀሳቀሰውን ወራሪ ቡድን መግታት ይኖርበታል ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ ምንም እንኳን አሸባሪ ቡድኑ በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ለመግባት ቢሞክርም ፣ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ በወረራ ከያዛቸዉ አካባቢዎች ተባሯል ብለዋል።
ቡድኑ በወረራ ይዟቸዉ በነበሩ አካባቢዎች መሠረተ ልማቶች በማዉደም ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ ንፁሃንን በግፍ መጨፍጨፉንም በመግለጫቸው ማስታወሳቸውን ኢፕድ አመላክቷል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.