Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ አራት ከተሞች የሚተገበር የዘመናዊ ካዳስተር ፕሮግራም ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮርያ መንግስት ትብብር በስዊዝ ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ አራት ትላልቅ ከተሞች የሚተገበር ዘመናዊ የመሬት መረጃ እና አስተዳደር ስርዓት ፕሮጀክት ተጀመረ።

የካዳስተር ስርዓት ጨምሮ ዘመናዊ የከተሞች መሬት መረጃና አስተዳደር፣ የአይሲቲ ግንባታ እና የአቅም ማሳደጊያ ስራዎችን የያዘው ፕሮጀክቱ ‘ኤል.ኤክስ.ጄ.ቪ’ በተሰኘ የደቡብ ኮርያ ድርጅት በቀጣይ 45 ወራቶች ይተገበራል ተብሏል።

ፕሮግራሙ በዘርፉ የረጅም ዓመት ውጤታማ ልምድ ያላትን ደቡብ ኮርያ ተሞክሮ ቀምሮ የያዘ በመሆኑ ÷ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ግንባታ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ሲሉ አቶ ፋንታ ደጀን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ገልፀዋል።

የደቡብ ኮርያ መንግስትም ተስፋ ሰጪ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት እንዲተገበር ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

የደቡብ ኮርያው ኤል.ኤክስ.ጄ.ቪ ድርጅት ፕሮጀክት ማናጀር ሚስተር ዩን ጁንግ ሁዋን በበኩላቸው ÷ በአፍሪካ ምሳሌ የሆነ እና የኢትዮጵያን የመሬት አስተዳደር በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲጣል የሚስችለውን ፕሮጀክት ለድርጅቱ ታምኖ በመሰጠቱ አመስግነዋል።

በቀጣይም በታሰበው ጊዜ ለመፈፀም እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

አዳማ፣ ሀዋሳ፣ ባህርዳርና መቀሌ ከተሞች በዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ሲሆኑ ÷ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 24 ሰዓት ዘመናዊ የመሬት መረጃ ስርዓትን የሚይዙ ሲ.ኦ.አር.ኤስ ማማዎች ተከላን ትግበራው ያጠቃልላል ተብሏል።

ጎህ ንጉሱ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.