Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር የስልጣን ርክክብ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ከሁሉም ነገሮች አስቀድሞ ሀገርን መታደግ እንደሚያስፈልግ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው ተናገሩ፡፡

ህብረተሰቡ በሁሉም አካባቢዎች ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበት የጠቆሙት ርዕሠ መስተዳድሩ÷ ህዝቡም እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

በተባበረ ክንድ መነሳት በሚያስፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን ያሉት አቶ እርስቱ ÷ የጁንታውን ሀሳብ ለማሳካት ለሚንቀሳቀሱ ሀይሎች እድል መስጠት አያስፈልግም ብለዋል፡፡

በደቡብ ክልል ምክር ቤት በመገኘት ባደረጉት ንግግርም÷ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመሆን ጥያቄ ሂደት ዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መካሄድ እንዲችል ክልሉ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

ይህም ሒደት ብዝሃነት ላላቸው ሀገራትም ምሳሌ መሆን የሚችል ተግባር ነው ብለዋል፡፡

አዲሱ ክልል በፍጥነት ወደ መሬት እንዲወርድ ለማድረግ በትኩረት መሰራት አለበትም ነው የተናገሩት፡፡

ከፋይናንስ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በኮሚቴ የሚታይና ለመንግስት የሚቀርብ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ከንብረት ክፍፍልና ከሰራተኛው ጋር የተያይዙ ጉዳዩችም በዝርዝር ከቀረበና ሀሳብ ከተሰጠበት በኋላ ሞሽኑ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡

በደቡብ ክልል ደረጃ ተመዝግቦና ተደራጅቶ የሚገኝ የፋይናንስ መረጃ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች እንዲሁም እዳዎች ለአዲሱ የሲዳማ ክልል ተጠናቆ ከተላለፉት ሀብትና ዕዳ ውጭ ያሉ ያልተጠናቀቁ የጋራ ሀብትም ሆነ ዕዳ ክፍፍል የደቡብ ክልል፣ የሲዳማ ክልል እና አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተገኙበት በጋራ ይከናወናል ነው የተባለው፡፡

የከፋ፣ የዳውሮ፣ የሸካ፣ የቤንች ሸኮ፣ የምዕራብ ኦሞ ዞኖችና የኮንታ ልዩ ወረዳ በአንድ ላይ ሆነው 11ኛው ክልል እንዲሆኑ በሕግ መፈቀዱ ይታወሳል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመሆን ጥያቄን ሂደት የሚያመላክት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በኋላ የስልጣን ርክክብ ተደርጓል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.