Fana: At a Speed of Life!

የኤል ሳልቫዶር የፀጥታ ሀይሎች የተሻለ የጦር መሳሪያ ለመታጠቅ ብድር እንዲፀድቅላቸው ወደ ፓርላማ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ የኤል ሳልቫዶር ፖሊሶችና ወታደሮች የተሻለ የጦር መሳሪያ እንዲታጠቁ ፓርላማው 109 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ብድር እንዲያፀድቅላቸው ወደ ፓርላማው ዘልቀው ገብተዋል።

ታጥቀው ወደ ፓርላማ የገቡት ፖሊስና ወታደሮች የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ናይብ ቡኬሌ ለምክር ቤቱ አባላት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ በነበረበት ወቅት ነው።

ቀደም ብሎ ፕሬዚዳንቱ የፓርላማው አባላት የ109 ሚሊየን ዶላሩን ብዱር በመደገፍ ውሳኔ እንዲያሳልፉ ሰባት ቀን ሰጥተዋቸው እንደነበረ ነው የተነገረው።

የኤል ሳልቫዶር ተቃዋሚ ፖለቲከኞችም የፀጥታ ሃይሎቹን ድርጊት ያልተለመደ የማስፈራሪያ ተግባር ሲሉ አውግዘውታል።

ሀገሪቱ ዓለም ላይ በሰዎች ግድያ ቀዳሚውን ደረጃ ከያዙት ሀገራት ተርታ ትገኛለች።

በኤል ሳልቫዶር ከሚፈፀሙት ግድያዎች ውስጥ በርካታዎቹ በማዕካላዊ አሜሪካ በተዘረጋው የወንጀለኞች ቡድን አማካኝነት እንደሚፈፀሙ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በፈረንጆቹ ሰኔ ወር 2019 ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዚዳንቱ የወንጀል ቡድኖችን ድርጊት እና ሙስናን ለመከላከል በወቅቱ ቃል ገብተው ነበር።

የ38 ዓመቱ ፕሬዚዳንት በሀገሪቱ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል በብድር የወታደሮችን እና ፖሊሶችን ትጥቅ ለማዘመን ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯል።

ፓርላው እንዲያፀድቀው የሚፈለገው ብድር የፖሊስ ተሽከርካሪዎችን፣ መለዮ፣ የክትትል መሳሪያዎች እና ሄሊኮፕተሮችን ለመግዛት ይውላል ተብሏል።

የፓርላማው አባላት ግን ባለፉት ሳምንታት በዚህ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ክርክር ለማድረግ እንደማይቀመጡ ሲገልፁ ቆይተዋል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.