Fana: At a Speed of Life!

የሽብር ቡድኑ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሰው በደል መቼም አይዘነጋም- የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትህነግ አሸባሪ ቡድን ባለፋት 27 አመታት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሰው በደል መቼም የሚዘነጋ አይደለም ሲሉ የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
 
ነዋሪዎቹ አሸባሪው ህወሃት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በመከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ የፈፀመውን ጭፍጨፋ አንደኛ አመትን በሻማ ማብራት ስነስርዓት አስበዋል።
 
በእዙ ላይ የተፈፀመው ክህደት መቼም የማንረሳው ህመም ነው፣ ጉዳቱም የሰሜን እዝ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነውም ብለዋል።
 
በዚህ ወቅት ሀሳባቸውን የሰጡን ነዋሪዎች አሸባሪዉ ቡድን ለትግራይ ህዝብ አካልና መከታ የሆነው የሰሜን እዝ ለይ ያደረሰው ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ ቡድኑ ቀድሞም ለራሱ ፍላጎትና ዘረፋ እንጂ ለህዝብ ምንም ደንታ የሌለው መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።
 
ሰሜን እዝ ለሀገር መከታና ለህዝብ አለኝታ ሆኖ ሳለ በዚህ ሰው በላ ቡድን ከኃላ ጥቃት ተፈፅሞበታል ይህ ደግሞ የቡድኑን አረመኔያዊ ተግባር ያሳያል ያሉት የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪዎች የሰሜን እዝ አባላት ግን ያለምንም ቅድመ ዝግጅት ጁንታውን ተከላክለው ሀገርን ከጥፋት የታደጉ ጀግኖች ናቸው ብለዋል።
 
አሁንም አሸባሪው ቡድን እኔ ካልመራው ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት ብሎ የክፋት በትሩን እያነሳ ነው ያሉት ነዋሪዎች ይህ ሀሳቡ ግን ኢትዮጵያውያን እያለን መቼም አይሳካለትም እኛም በተባበረ ክንድ የጁንታውን ህልም ከንቱ ለማድረግ ለመከላከያ ሰራዊት የምናደርገውን ድጋፍ በቁስ በመንፈስና በግንባርም በመዝመት የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አጋግጠዋል።
 
ቡድኑ በስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን ህዝብን በመከፋፈል እርስ በርሱ እንዲጠራጠር በማድረግ የኢትዮጵያን ልጆች ደም ሲመጥ ነበር ያሉት ነዋሪዎች የኦሮሞ ህዝብም ልክ እንደሌሎቹ ወንድሞቹ ሀሉ ልጆቹን ሲገብርና ዋጋ ሲከፍል ነበር ብለዋል።
 
ይህ ቡድን ካሁን በኃላ በኢትዮጵያ እድል እንዲኖረው በፍፁም አንፈቅድም ብለዋል።
የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ዎሾ ከድር የሰሜን እዝ ላይ የደረሰው ጥቃት መቼም የማይረሳ ክህደት ነው ይህ ቀን የህዝብ ልጅ የሆነውና ህዝብ በህወት እንዲኖር ለራሱ ሳይሳሳ ለኛ የሚሞተው ሰራዊት የከዳበት ቀን በመሆኑ ይህ ሀገር እስካለ ድረስ ታሪክ ያወሰዋል ብለዋል።
 
አሁንም የከተማው ነዋሪዎች ከትንሽ ገንዘብ ጀምሮ በአካል እስከመዘመት ድረስ የጀመራችሁትን አጠናክራችሁ መቀጠል አለባችሁ ያሉት ከንቲባው አካባቢያችን ነቅተን መጠበቅ ደግሞ የጁንታውን ሀሳብና ሴራ ማክሸፊያ መንገድ ነው ብለዋል።
 
ጥላሁን ይልማ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.