Fana: At a Speed of Life!

ህልውናችን ለማረጋገጥ የጋራ መስዋዕትነት እንከፍላለን እንጅ በጠላት እጅ እየሞትን መኖርን ፈጽሞ አንፈቅድም- አቶ ግዛቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህልውናችን ለማረጋገጥ የጋራ መስዋዕትነት እንከፍላለን እንጅ በጠላት እጅ እየሞትን መኖርን ፈጽሞ አንፈቅድም አሉ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኅላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ፡፡
 
አቶ ግዛቸው ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
ያስተላለፉት መልዕክት እንደሚከተለው ይቀርባል፡-
 
የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት ብሎም የኢትዮጵያ ደመኛ የሆነው የትግራይ ወራሪ ኃይል ዓላማና ግቡ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ መነሻው አማራን እንደ ሕዝብ ማጥፋት ብሎም ኢትዮጵያን እንደ ሀገር እና የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደ ሕዝብ በመበታተን ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ በተግባር እያየነውና እየሆነ ያለ እንጂ ትናንት የሆነ እና ወደፊት ሊሆን የሚችል በሚል የሚገለጽ ብቻ አይደለም፡፡
 
ለዚህም አሁን እየፈጸመ ያለው ወረራ፣ ዘረፋ፣ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እና የሃብት ንብረት ውድመት ወንጀል ከምስክርነት በላይ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የጀመርነው የህልውና ዘመቻ ነጻነታችንን ተነፍገን ሞታችንን ተለማምደን የምንኖርበት ሳይሆን ለመሞት ወስነን ጠላትን ድል አድርገን ታሪካችን የምናድስበት የመጨረሻ ምርጫችን ነው፡፡
 
ከትግራይ የተነሳው ወራሪ ኃይል ስልጣን ላይ በቆየበት ዘመን በስውርና በሴራ በአማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ተዘርዝሮም ሆነ ተተርኮ አያልቅም፡፡ ይህ ቡድን በሕዝብ መራር ትግል ከስልጣን ተገፍቶ መቀሌ ከተወረወረ በኋላ ከስውርና ከሴራ ጅምላ ግድያው ተላቆ በግላጭ በአማራ ሕዝብ ላይ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ባሰማራቸው ተላላኪዎቹ አማካኝነት ሳይቀር ዘግናኝ ጭፍጨፋ ፈጽሟል፡፡
 
በአማራ ሕዝብ ላይ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ፤ ለህሊና የሚከብዱ ዘግናኝ ሰቆቃዎችን ፈጽሟል፡፡ በማይካድራ፣ በአጋምሳ፣ በጭና፣ በቆቦ፣ በወልድያ፣ በመርሳ፣ በሐይቅ፣ በደሴ፣ በኮምቦልቻ፣ ወጣቶች እና ሴቶች ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ዘግናኝ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ፈጽሟል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ጅምላ ጭፍጨፋ ብቻ ሳይሆን በሰው ልጅ ሊፈጸም የማይችል ግፍ በመፈጸም በአማራ ላይ ያለውን የጭካኔ ጥግ በተግባር አሳይቷል፡፡
 
ይህ የጠላት ኃይል እግሩ በረገጠው የአማራ ምድር ሁሉ እናት እና አባት ዓይናቸው እያዬ ያሳደጓት ሴት ልጅ ወራሪው የትግራይ ኃይል በቡድን ደፍሯል፡፡ በቡደን ከመድፈር ባሻገር ሕጻን፣ ወጣትና አዛውንት ሳይል እንዲሁም የጾታ ልዩነት ሳይገድበው በጅምላ ጨፍጭፏል፡፡ በመርሳ 20 በላይ የሚሆኑ ወጣቶችን በአንድ ክፍል ዉስጥ ዘግቶ፣ ተቀጣጣይ ፕላስቲክ አልብሶ ፤ ቤንዚን አርከፍክፎ አቃጥሏል፡፡ በዓለማችን ላይ የሰው ልጅ በሰው ላይ ሊፈጽመው ይችላል ተብሎ የማይታሰብ ሰውን ለእርድ እንደ ቀረበ እንስሳ እንገቱን በቢላ ቆርጦ ቆዳውን ገፏል፡፡ ይሄ በአደባባይና በተግባር በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸመ መራራ እውነት ነው፡፡
 
ከሰብዓዊነት በተጨማሪ የአማራ ሕዝብ የሚገለገልባቸውን አንጡራ ሃብቶች በጅምላ ከመዝረፍ ባሻገር ሊጠቅሙ ይችላሉ ያላቸውን ሀብቶች አውድሟል፡፡ ክላሽና ስናይፐር ይዘው የማይዋጉትን የቤት እንስሳትን ሳይቀር በጥይት ተኩሶ ጨፍጭፏል/ገድሏል፡፡በርካታ ንጹሐንን በጅምላ ጨፍጭፏል፡፡
 
በእብሪት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ሁሉ ለአማራ ሕዝብ ሊጠቅሙ ይችላሉ ብሎ ያሰባቸውን ህይወታዊ እና ቁሳዊ ሀብቶቹን በሙሉ አውድሟል፤ ዘርፏል፡፡ የደረሱ ሰብሎችን ሳይቀር አጭዶ ወደ ትግራይ ጭኗል፡፡ ያልደረሱ ሰብሎችን ነገ ሊጠቅሙ ይችላሉ በሚል እሳቤ አውድሟል፡፡ ለአማራ ካለው ጥላቻ የተነሳም ባህሉን፣ እምነቱን፣ ወጉንና ሥነልቦናውን ሳይቀር ለመሸርሸር ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ ሠርቷል፡፡
 
በመሆኑም እንደሕዝብ ለማጥፋት በጋራ የመጣን ወራሪ ጠላት ህልምና ምኞቱን ማክሸፍ የሚቻለው አንደ ሕዝብ በጋራ አንድ ሁነን በመቆም ነው፡፡ ከአሁን በኋላ እንደሕዝብም ሆነ እንደ ሀገር ህልውናችን ለማረጋገጥ የጋራ ትግልና መስዋእትነት እንከፍላለን እንጂ እየሞትን ለመኖር ለአሸባሪ ቡድን በርም ሆነ እድል አንሰጥም፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡
 
የትግራይ ወራሪ ኃይል የአማራን ሕዝብ ትናንትም ሆነ ዛሬ ፤ ነገና ወደፊትም እየገደልሁህ፣ መሞትህን አምነህ ተቀብለህ ትኖራለህ ብሎ ዓይኑን በጨው ታጥቦ በጅምላ መጨፍጨፉን አላቋረጠም፡፡
 
ስለሆነም እንደበግ እያረደ ለማጥፋት የተነሳን ወራሪ ጠላት ማጥፋት ብቸኛው ምርጫ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ መፍትሔው አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ እየሞቱ ከመኖር ይልቅ ዘር ጨፍጫፊንና ሞትን “ሆ” ብሎ እንደ ሕዝብ በጋራ ድል መንሳት ነው፡፡
 
ትናንትን ከመውቀስ ይልቅ ነጋችን ላይ አንድ ሁነን ጠላትን በጋራ መቅበር ግድ ይለናል፡፡ በአንድነት ከተነሳን ከፊት ለፊታችን የተደቀነውን የህልውና አደጋ በጋራ በመቀልበስ ብቻ ሳይሆን ወራሪውን ኃይል በአጭር ጊዜ እስከወዲያኛው እንደምንቀብረው ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለንም፡፡ ድል ያለምንም ትግልና መስዋእትነት አይገኝም፡፡ ድል የሚገኘው በጀግነነትና በቆራጥነት በሚከፈል ብርቱ መስዋእትነት ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ወራሪውን ቡድን በጋራ መቅበር ካልተቻለ ከዚህ በፊት ከፈጸማቸው ግፍ የተሞላበቻው ጅምላ ጭፍጨፋዎች በላይ ነገ የከፋ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
 
ስለሆነም እንደሕዝብም ሆነ እንደ ሀገር ህልውናችን የሚጸናው በትግራይ ወራሪ ኃይል መቃብር ላይ ነው ስንል ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ ሳይሆን ጠላት ይዞት የተነሳው አቋም የአማራን ሕዝብ እንደሕዝብ በማጥፋትና ኢትዮጵያን ሀገር በማፍረስ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው፡፡ ህልውናችን ለማረጋገጥ የጋራ መስዋእትነት እንከፍላለን እንጅ በጠላት እጅ እየሞትን መኖርን ፈጽሞ አንፈቅድም! ብቸኛው ምርጫችንም ጠላትን ማሸነፍና በአንድነት ተሰልፈን በመቅበር የአማራንም ሆነ የኢትዮጵያን ትንሣኤ እውን ማድረግ ነው፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.