Fana: At a Speed of Life!

የእብናት ወረዳ ዘማቾች ሽኝት ተደረገላቸዉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ ነዋሪዎች የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ ተቀብለው አሸባሪውን ቡድን ለመፋለም ወደ ጦር ግንባር እየዘመቱ ነው።

አሸባሪውና ወራሪው ቡድን በአማራ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍና መከራ ሊበቃ ይገባል፤ከእንግዲህ በኋላ አሸባሪውና ወራሪውን የትግራይ ኃይል የሚሸከም ትክሻ የለንም፤ አርሶ አደሩ ማምረትና ወልዶ ማሳደግ የሚቻለው የአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኃይል ግብዓተ መሬት ሲፈጸም ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ቡድኑ ሴቶችን እየገደለ፣ እየደፈረ እና የአርሶ አደሩን ሀብት እየዘረፈ መኖር የለበትም ብለዋል፡፡

ይህንን ወራሪ እና ሽብርተኛ ኃይል በአጭር ጊዜ ድባቅ በመምታት ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ነፃ ለማውጣት በቁርጠኝነት መነሳታቸውን ተናግረዋል።

ነፃነቷን ጠብቃ ለዘመናት የኖረችውን ኢትዮጵያ በጡት ነካሹና አሸባሪው ቡድን ተወራለች፤ ሕዝቡ ከጫፍ እስከጫፍ በአንድነት ከተነሳ ግን አሸባሪ ኃይሉን በአጭር ቀን መደምሰስ ይችላል፤ለዚህም በነቂስ መነሳታቸውን ገልጸዋል፡፡

የእብናት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሙሉጌታ ይማም በበኩላቸዉ÷ ነጻነቷ ሉዓላዊነቷ እና ክብሯ የተጠበቀ ሀገር ከአያቶቻችን እንደተረከብን ለሚቀጥለው ትውልድም ከነጻነቷ፣ ሉዓላዊነቷ እና ክብሯ ነው ልናስረክብ የሚገባው ብለዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው ሕዝቡ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ተፋልሞ ነጻ እንዳይወጣ የሐሰት ወሬ በሚያናፍሱ የውስጥ ባንዳዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ ይወሰዳል፤ እንዲህ ዓይነት ተግባር ላይ የሚሳተፉ አካላትም ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.