Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መከረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በክልሉ ከሚገኙ አጠቃላይ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ በውይይት መድረኩ ላይ ፥ አሸባሪው የህወሓት ቡድን እና ተላላኪዎቹ ኢትዮጵያን እኔ ካልመራዋት ትፍረስ ትበታተን የሚል አላማን አንግበው እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም ሁሉም አመራር ይህንን ተገንዝቦ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ በከፍተኛ ቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ካልዘረፈ መኖር የማይችለውና የእኩልነት ቋንቋ የማይገባው ቡድኑ እየፈጸመ ያለው ጥቃት ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ዳግም የማዋረድ መሆኑን ገልጸው ፥ ይኸም የሞት የሞቱን የሚያደርገው መፍጨርጨር የመጨረሻ መሆኑንም አውስተዋል።
ይህን የተደቀነብንን ሀገር የማፍረስ አደጋ ለመቀልበስ ሁሉም አመራር ተቀናጅቶ ፣ ተናቦ እና የተግባር አንድነት ፈጥሮ ሀገርን ከብተና ኢትዮጵያዊያንን አገር አልባ ከማድረግ ክፉ ምኞት መታደግ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
መላው የክልሉ ነዋሪዎች እንደከዚህ ቀደሙ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እና ሌሎች የጸጥታ አካላትን በሞራል እና በሎጅስቲክ በመደገፍ ደጀንነቱን ማሳየት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
አመራሩ በሃገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል የወጣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመፈጸም እና የማስፈጸም ግዴታ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ በበኩላቸው፥ ወጣቶችም እንደከዚህ ቀደሙ የመከላከያ ሰራዊቱን በመቀላቀል ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለበትን ሀገራዊ ለውጥ በፅንፈኛ ቡድኖች እንዳይቀለበስ መታገል እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ህዝብን ባሳተፈ መልኩ የአሸባሪውን ተላላኪዎች በተደራጀ መንገድ በማጋለጥና አሳልፎ በመስጠት የአካባቢዉን ሰላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎንም በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመደገፍ እና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በትኩረት መሰራት እንደሚገባም ሀላፊው ገልጸዋል።
አመራሮቹም በበኩላቸዉ አመራርነት ከኃላ መከተል ሳይሆን ከፊት ሆኖ መምራት ነዉ ፣ ህዝባችንን አስተባብረን እና በአካልም በግንባር በመገኘት ኢትዮጵያን ለማዋረድ የሚመጣዉን ጁንታ ለአንዴና ለመጨረሻ ለመደምሰስ ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
9
Engagements
Boost Post
9
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.