Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ለተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የስራ ስምሪት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ለባለድርሻ አካላት በዛሬው ዕለት ማብራሪያ እና የስራ ስምሪት ተሰጥቷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን፣ በአገር ደረጃ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሻ በማድረግ ለባለድርሻ አካላት ማብራሪያ እና የስራ ስምሪት በመስጠት ወደ ሥራ እንዲገቡ አቅጣጫ መስጠታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በተለያዩ አካባቢዎች የውስጥና የውጭ ባንዳዎችን በማደራጀት ሃገር ለማፍረስ የሞት ሽረት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የጥፋት ቡድኑን እኩይ ተግባር ለማክሸፍ ኮሚቴው ከወትሮው በተለየ ትኩረትና ዝግጅት ሥራውን ማስፈጸም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የዜጎችን ህልውና ለመታደግ የክልሉ መንግስት ያስቀመጠው አቅጣጫ ወቅታዊ መሆኑን የጠቆሙት የግብረ ኃይሉ አባላት በበኩላቸው÷ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በሙሉ ቁርጠኝነት ለማስፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.