Fana: At a Speed of Life!

የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለነበሩ ተማሪዎች ጊዜያዊ ምደባ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር በመቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ ራያ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ ለነበሩ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ምደባ አካሄደ።
ሚኒስቴሩ በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ ተማሪዎቹ የተመደቡባቸውን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቀጥሎ ባለው አድራሻ https://www.placement.ethernet.edu.et/ ማየት እንደሚችሉ አስታውቋል።
ተማሪዎቹ የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ጥሪ ሲያደርግላቸው ብቻ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንዲያደርጉም መልዕክት አስተላልፏል።
ምደባው እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. የነበረውን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን ጨርሰው የወጡ ተማሪዎችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን፥ ምደባው መረጃዎችን በትክክል ላስገቡ ተማሪዎች ብቻ የተካሄደ መሆኑንም ገልጿል።
መረጃዎችን በትክክል ያላስገቡ እና የኦን ላይን ፎርሙን በተለያየ ምክንያት በወቅቱ መሙላት ያልቻሉ ተማሪዎች ስማቸውን ኦንላይን ምደባ በሚረጋገጥበት ሶፍትዌር ላያገኙ ስለሚችሉ በነበሩበት የትምህርት ክፍልና ዩኒቨርሲቲን መነሻ በማድረግ በዲፓርትመንት የተመደቡ በመሆኑ የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸውም ነው የገለጸው።
ተመዝግበው ሳይመደቡ የቀሩ ተማሪዎችም በቂና ግልፅ መረጃ ባለማቅረባቸው ምክንያት ያልተመደቡ መሆኑን አውቀው፥ የትምህርት ክፍላቸው በተመደበበት ዩነቨርሲቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉም አሳስቧል።
ያልተመዘገቡ እና ቅሬታ ወይም አቤቱታ ያላቸው ተማሪዎች በተቀመጠው የቴሌግራም ቦት አድራሻ (@moeplacementbot) ብቻ አቤቱታቸውን እንዲያቀርቡም ጠይቋል።
በፈቃድ እረፍት (Withdrawal) ላይ የነበሩ ተማሪዎችም የትምህርት ክፍላቸው ለተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ማስረጃቸውን አቅርበው እንደሚታይላቸው መግለጹን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.