Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ የጦር መሳሪያ ያላቸው ግለሰቦች ምዝገባ እያካሄዱ ነው-ዶ/ር ቀነዓ ያደታ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የጦር መሳሪያ ያላቸው ግለሰቦች ምዝገባ እያካሄዱ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ገለጹ።
የመዲናዋ ነዋሪዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የከተማዋን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ እያስጠበቁ መሆኑንም ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጦር መሳሪያ ያላቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች ምዝገባ እንዲያካሄዱ አቅጣጫ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ምዝገባው ዛሬ ይጠናቀቃል።
የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ለኢዜአ እንደገለጹት ፥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው።
ከዚህ አኳያ የጦር መሳሪያ ያላቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች ምዝገባ ተጠቃሽ ነው።
በዚህም በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በርካታ ነዋሪዎች ምዝገባውን እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው ፥ በወረፋ ምክንያት ምዝገባው ዛሬ የማይጠናቀቅ ከሆነ ተጨማሪ ቀነ ገደብ ሊሰጥ እንደሚችል ጠቁመዋል።
በተያያዘ አሸባሪው ህወሃትና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የቡድኑ ደጋፊዎች የሀሰት መረጃ በማሰራጨት ዜጎች ተረጋግተው እንዳይኖሩ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም በዋናነት ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሆነው የአሸባሪ ቡድኑን እኩይ ዓላማ እንዳይመክቱ ትኩረት ለማስቀየስ መሆኑን ነው ዶክተር ቀነዓ የተናገሩት።
ከዚህ አኳያ የመዲናዋ ነዋሪዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የከተማዋን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ እያስጠበቁ መሆኑንም ነው ያነሱት።
በቀጣይም የጸጥታ አካላት የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ኀብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ነቅተው መጠበቅና የተለየ እንቅስቃሴ ሲመለከቱ ደግሞ በአቅራቢያቸው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት በመጠቆም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ነው መልእክት ያስተላለፉት።
በመዲናዋ በየደረጃው ላሉ አመራሮች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ ግንዛቤ የመፍጠር ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ቀነዓ ፥ የአዋጁን ይዘትና የአፈጻጸም ሂደት በተመለከተ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ውይይት እንደሚደረግም ተናግረዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of one or more people
0
People reached
54
Engagements
Distribution Score
Boost Post
53
1 Share
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.