Fana: At a Speed of Life!

የሰሜን ሸዋ ፋኖ እና ሚሊሻ አባላት ወደ ጦር ግንባር እየዘመቱ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ሸዋ ፋኖ እና ሚሊሻ አባላት የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ ተቀብለው አሸባሪውን ቡድን ለመፋለም ወደ ጦር ግንባር እየዘመቱ ነው።
ወደ ግንባር ሽኝት የተደረገላቸው የፋኖ እና ሚሊሻ አባላት የሸዋ ህዝብ ከአያት ቅድመ አያቶቹ የወረሰውን ጀግንነት ተላብሰው የሀገር ዳር ድንበር የማስከበር አደራን አንግበዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሀኑ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ዘማች የፋኖ እና ሚሊሻ አባላቱ አሸባሪውን ለመቅበር ና በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ ለማቆም በቁጭት እና ወኔ ተሞልተው ዘምተዋል ብለዋል።
የአማራ ህዝብ ከተጋረጠበት አደጋ ለመሻገር መደራጀት እና መዝመት ይጠበቅበታል ያሉት ሀላፊው የሸዋ ፋኖ እና ሚሊሻ አባላት ዘመቻ የህውሀት መጨረሻ እስትንፋስ እስትቋረጥ ይቀጥላልም ብለዋል።
በኤልያስ ሹምዬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person, sitting and outdoors
0
People reached
79
Engagements
Distribution Score
Boost Post
74
2 Comments
3 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.