Fana: At a Speed of Life!

የሰበታ ከተማ ነዋሪዎች ህልውናን ለማረጋገጥ ወያኔን ማጥፋት ይገባል አሉ

 አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኖቹን ህወሓት እና ሸኔን አገር የማፍረስ ሴራ የሚያወግዝ ሰልፍ በሰበታ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በሰላማዊ ሰልፉ የሽብር ቡድኖቹን አገር የማፍረስ ሴራ የሚያወግዙ እና የህልውና ዘመቻውን የሚደግፉ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡
በሰልፉ ወያኔ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላት ናት፣ እዘምታለሁ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አስከብራለሁ፣ በከሃዲዎች መቃብር ላይ የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን፣ የሽብር ቡድኑን ህወሓት ማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ ነው፣ የሸኔና የወያኔ የጭካኔ እርምጃዎችን አጥብቀን እናወግዛለን የሚሉ መፈክሮች ተደምጠዋል፡፡
በአፈወርቅ አለሙ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.