Fana: At a Speed of Life!

ቄሮና ቀሬ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተዋል –የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት በድንጋይና በዱላ አሸባሪውን ሲፋለም የነበረ ቄሮና ቀሬ ዛሬ ዘመናዊ ጦር መሣሪያ በመታጠቅ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መቆማቸውን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፥ አሸባሪው ሕወሓት ደደቢት በረሃ ከገባ ጀምሮ የሀገር ሉዓላዊነትና አንድነትን ከቻለ ማፍረስ ካልቻለ ለማተራመስ አቅዶና በማኒፌስቶው አካቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።
አሸባሪው ቡድን ሥልጣን ከያዘበት ዘመን ጀምሮ የሀገሪቱን ሕዝቦች በትናንሽ ልዩነቶች በመከፋፈልና በማባላት የተዳከመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር አልሞ ሲሠራ መቆየቱን የገለጹት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው፥ የሀገሪቱን መከላከያ ሠራዊት በመበተንና የአንድ ብሄር የበላይነት የሰፈነበት የመከላከያ ሠራዊት በመገንባት የተዳከመች ሀገር ለመፍጠር መሞከሩን ተናግረዋል።
ሃላፊው አያይዘውም በኢኮኖሚውም በኩል በዓለም ዓቀፍ ፋይናንስ ተቋም መረጃ መሠረት የተቆናጠጠውን ሥልጣን በመጠቀም 30 ቢሊየን ዶላር በመዝረፍ የኢትዮጵያን ካዝና ባዶ አስቀርቷል ብለዋል።
በሀገሪቱ የሚገኙ እስር ቤቶች አፋን ኦሮሞ የሚነገርባቸው እስከሚመስሉ ድረስ የኦሮሞ ወጣቶችን በስፋት ሲያስር ቆይቷልም ነው ያሉት።
ከሥልጣን ከተባረረ በኋላም በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ያልተረጋጋ ክልል እንዲሆን የተለያዩ ሴራዎችን ሲያቀነባብር መቆየቱን አቶ ኃይሉ ተናግረው፥ በመጨረሻም ሀገሪቱን ለመበተን በማሰብ የሰሜን ዕዝን ከኋላው በመውጋት አሳፋሪ ታሪክ መሥራቱን ጠቁመዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.