Fana: At a Speed of Life!

የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል የኢትዮጵያን ህልውና ማስጠበቅ እንደሚገባ የድሬዳዋ ከንቲባ ተናገሩ

 አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን ህወሓት የሚያወግዝ እና የአገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል።
የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የሽብር ቡድኑን ተግባር በማጋለጥ ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
አገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ የምትፈልገን ወቅት ላይ ነንና አካባቢያችንን በንቃት በመጠበቅና ፀጉረ-ልውጦች ሲያጋጥሙን ለፀጥታ አካላት በመጠቆም እንዲሁም ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በትብብር መንፈስ በመስራት የድርሻችንን መወጣት ይኖርብናልም ነው ያሉት፡፡
ከምንም በላይ ደግሞ አቅሙ ያለን የእናት አገር ጥሪን በመቀበል በአገራችን ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን ጁንታው ህወሓትን ለመገርሰስ በመዝመት ከአገራችን ጎን መቆም አለብን ብለዋል ከንቲባው።
በሰልፉ አሸባሪውን ቡድን የሚያወግዙ የተለያዩ መፈክሮች መስተጋባታቸውን ከድሬዳዋ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.