Fana: At a Speed of Life!

በአገር ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል የበኩላችንን እንወጣለን – የምክር ቤት አባላት

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገር ሕልውናና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል ተግባራዊ የሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈጻሚነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ።

የምክር ቤቱ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በኢትዮጵያ ላይ የተከፈቱ የወታደራዊ፣ የምጣኔ ሃብትና የፕሮፓጋንዳ ጦርነቶች የአገር ሕልውናን እንደሚፈታተኑ ገልጸዋል።

እነዚህ ሃይሎች ከሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተሻርከው በውግንና እየሰሩ ያለውን ተግባር ለመቀልበስ የጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያለውን ፋይዳም አንስተዋል።

ምክር ቤቱም የሕዝብ ተጠሪ እንደመሆኑ የጸደቀውን አዋጅ ተግባራዊ በማድረግ ሂደት የአባላቱ ሚና ግንባር ቀደም እንደሚሆን ገልጸው እንደ ምክር ቤት አባልና እንደ ዜጋም የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለም የተለያዩ አካላት የተለያዩ አስተያየቶችን ቢሰጡም በኢትዮጵያ ጉዳይ ከዜጎቿ በላይ ወሳኝ ሊሆኑ እንደማይችሉ ተናግረዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ቀደም ሲል በነበሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች የመርማሪ ቦርድ አባል ስብጥር የፓርቲ ማዕከላዊነት ይንጸባረቅ እንደነበረርአስታውሰዋል።

የምክር ቤቱ አባላት ኢትዮጵያውያን በአገራቸው አንድነትና ሕልውና ላይ አደጋ የደቀነውን የሽብር ቡድን ለመደምሰስ እያደረጉ ያለውን ተጋድሎ እንዲያጠናክሩም ጠይቀዋል።

የውስጥ አንድነትን በማጠናከር የውጭ ጫናዎችን መቋቋም እንደሚቻልም ማመላከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.