Fana: At a Speed of Life!

የአሸባሪውን ቡድን ቀብር በማፋጠን ወደ ልማት መዞር አለብን – የምዕራብ አየር ምድብ አዛዥ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪውን ቡድን ቀብር በማፋጠን ወደ ልማት መዞር አለብን ሲሉ የምዕራብ አየር ምድብ አዛዥ ገለጹ ።

በአየር ኃይል የምዕራብ አየር ምድብ የሰራዊት አባላትና ሲቪል ሰራተኞች አሸባሪው ሕወሓት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት በሰሜን ዕዝ አመራርና የሠራዊት አባላት ላይ የፈፀመው አረመኔያዊ ጥቃት አንደኛ አመት በተለያየ ዝግጅት አስበው ውለዋል ፡፡

በዚህ ወቅት አዛዡ ኮሎኔል ቸርነት መንገሻ ÷የሕወሓት አሸባሪ ቡድን ከምስረታው ጀምሮ ለአገር ደንታ የሌለው ሽፍታ ቡድን መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የምድቡ ሰራዊት ይህን ተገንዝቦ አሸባሪውን በመቅበር ወደ ልማት መዞር አለብን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.