በትምህርት ዘርፉ የኮቪድ-19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርት ዘርፉ ውስጥ የኮቪድ-19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ከሚመለካታቸው አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።
የኮቪድ-19 ስርጭትን በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለመቀነስ ክትባቱ ለመምህራን እና በትምህርት ዘርፉ ላይ ለሚሰሩ አካላት ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በመድረኩም የኮቪድ -19 ክትባትን በትምህርት ዘርፉ በተለይ በትምህርት ቤት እና ዩኒቨርስቲዎች ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁም ተነግሯል።
በቀጣይ ዘመቻ በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንን የመከተብ ስራ እንደሚሰራ ነው የተገለፀው።
በተጨማሪም በኮቪድ-19 ክትባት ላይ ያለውን የተዛባ ግንዛቤም ለማሻሻል ትምህርት ቤቶች ላይ በቀጣይነት መሰራት እንዳለበትም መገለፁን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!