Fana: At a Speed of Life!

የህወሓትን ጦርነት ለመቀልበስ እንዘምታለን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን የከፈተውን ጦርነት በመቀልበስ ኢትዮጵያን በማዳኑ ዘመቻ ለመሳተፍ ወደ ግንባር እንደሚዘምቱ የጋምቤላ ከተማ ወጣቶች ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቢፍጨረጨርም÷ እንደማይሳካለት ነው ወጣቶቹ የተናገሩት፡፡
ህወሓት ግብረአበሮቹን ከውጭ ጭምር በማምጣት ሀገር ለማፍረስ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያን እኔ ካልመራሁ አትኖርም በሚል ሀገር ለማፍረስ የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስና ሀገር ለማዳን የማንዘምትበት ምክንያት አይኖርምም ነው ያሉት ወጣቶቹ፡፡
ከጉያችን ስር ሆነው ለአሸባሪው ቡድን የሚላላኩ ቅጥረኞችንም አጋልጦ ለመስጠት ዝግጁ ነን፤ መንግስትም የህዝብን ጥቆማ በመቀበል ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡
ለሀገር ዘምቶ መሞት አኩሪ ታሪክ በመሆኑ÷ የአሸባሪዎችን ሀገር የማፈረስ ሴራ ለመቀልባስ ወደግንባር እንዘምታለን ሲሉ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡
በክልሉ እየተስፋፋ ያለው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለአሸባሪዎቹ ተላላኪዎች እኩይ ተግባር ማስፈፀሚያ ሊውል ስለሚችል÷ ችግሩን ለመግታትም መንግስት ጠንክሮ እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.