Fana: At a Speed of Life!

ከደጀን እስከ ግንባር መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን – የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደጀን እስከ ግንባር ለአገራችን መክፈል የሚገባንን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ፡፡
በመዲናዋ የሚገኙ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህልውና ዘመቻ ላይ የጀመሩትን እንቅስቃሴ ለማቀናጀት የሚያስችል የውይይት መድረክ አካሂደዋል።
በታሪካዊ የትግል ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ያሉት የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ ÷ ሁላችንም ያለችንን አንድ ሀገር ከወራሪ ጠላት የማዳን የጋራ ሃላፊነት አለብን ብለዋል።
አንድ ላይ ቆመን በመፋለም ታሪካዊ ድል ከማስመዝገብ ውጭ ሌላ አማራጭ የለም ያሉት አቶ መለሰ፥ ለመላው ኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላት የሆነው አሸባሪ ቡድን መደምሰስ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ከዚህ አሸባሪ ሃይል ጀርባ ብዙ ተዋናይ መኖራቸውን በመጥቀስም የእነዚህን ያልተገባ አካሄድ በመግራት ሉዓላዊ ክብራችንን ለማስጠበቅ በጋራ መስራት ይገባናል ነው ያሉት።
አገርን ከጠላት መጠበቅ የመንግስት ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሃላፊነት መሆኑን የገለጹት የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች÷ የተከፈተብን ጦርነት እንደ ህዝብ ነውና አንድ ላይ በመሆን እንደ ህዝብ ተደራጅተን መመከት ይገባናል ሲሉም አንስተዋል።
ስልጣን በምርጫ እንጂ በጦርነት አይመጣም ያሉት አመራሮቹ÷ ሊያጠፋን የመጣውን አሸባሪ ሃይል አቅማችንንና ሃይላችንን በማሰባሰብ ወደዚህ ሃይል መዝመት አለብን ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.