Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከ3 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከ3 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ነገ እንደሚያስመርቅ የዩኒቨርስቲው የዓለምአቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አስታወቁ።

ዩኒቨርሲቲው ለ13ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከሚስመርቃቸው ተማሪዎች መካከል 1 ሺህ 6ቱ ሴቶች ናቸው።

የዩኒቨርስቲው የዓለምአቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጋንፉሬ እንደገለጹት፥ ዩኒቨርሲቲው በመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 559 ተማሪዎች በመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ ነው የሚያስመርቀው።

ዩኒቨርሲቲው ነገ በሚካሄደው የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የፌደራልና የድሬዳዋ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የዩኒቨርስቲው የቦርድ አመራሮች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሙሩቃን ቤተሰቦች እንደሚታደሙ ከወጣው መርሀ ግበሩ ለማወቅ ተችላል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በ1999 ዓ.ም ከተቋቋሙት የሁለተኛው ትውልድ ዩኒቨርስቲዎች መካከል አንዱ ሲሆን÷ እስካሁን በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በተለያዩ የሙያ መስኮች አሰልጥኖ ያስመረቀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.