Fana: At a Speed of Life!

ራሳችንን ነፃ ለማውጣትና ታሪካችንን ለመጠበቅ የምንሰስተው ሕይወት አይኖርም- የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ራሳችንን ነፃ ለማውጣት፣ ክብራችንና ታሪካችንን ለመጠበቅ የምቆጥበው ጉልበት፥ የምንሰስተው ሕይወት አይኖርም ሲሉ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱ ሁሴን ተናገሩ።

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳደሪ ለአሚኮ እንደገለጹት፥ አሸባሪውና ወራሪውን የትግራይ ኃይል ለማጥፋት የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ፣ ሚሊሻና መላው ሕዝብ እየታገለው ነው።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በወሎ ምድር ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች ወገኖችን እየገደለ፣ ንብረት እየዘረፈ፣ ተቋማትን እያወደመ፣ የአርሶ አደሩን ሰብል እየወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።

አሸባሪው ኃይል አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት የዞኑና የክልሉ ህዝብ ራሱን አደራጅቶ ትግሉን ማጠናከሩንም አስታውቀዋል።

የዞኑ አስተዳደር በየወረዳው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተዋጊ በማሰማራት ጠላትን ለመደምሰስ እየሠራ መሆኑንም ገልፀዋል።

ወራሪውንና ዘራፊውን ቡድን ከወረራቸው አካባቢዎች ነቅሎ ለመጣልና በሌላ ጊዜም ስጋት እንዳይሆን ለማድረግ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በዚህም በቅርብ ቀን ውጤት እንደሚያስመዘግብም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል። ከሌሎች ዞኖች የተውጣጡ ኃይሎችም በዞኑ መሠማራታቸውን ተናግረዋል።

ጠላትን ለመደምሰስ በሚደረገው ትግል ሁሉም ወገን ሀብትና ንብረቱን ከዚያም አልፎ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚደርስ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን ነው ያሉት።

መንግሥት ባስተላለፈው የክተት ጥሪ መሠረት ሁሉም የሰው ኃይል፣ ሀብትና ንብረት ወደ ግንባር መሆን አለበት ነው ያሉት።

ጠላት እየተጠቀመ ያለው ስልት አሉባልታና የሀሰት ወሬ መበተን፣ መሪ እንዳይኖር ማድረግ፣ በውስጥ ገብቶ መሸርሽር ነው ያሉት አቶ አብዱ፥ የጠላትን እንቅስቃሴዎች ማምከን ከቻልንና መተባበር ከቻልን ጠላትን መደምሰስ እንችላለን ብለዋል።

መደማመጥ፣ መተባበር እና ትክክለኛ መረጃዎችን ከትክክለኛው ምንጭ በመውሰድ በዚያ ላይ የተመሰረተ የተግባር ትንተና መስጠት እንደሚገባም ጠይቁመዋል።

የማኅበራዊ አንቂዎችና የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የጠላትን ዓላማና አረመኔያዊ ተግባራት በማጋለጥ ሕዝቡ ጠላት ላይ ያለው እይታ እንዳይከፋፈል ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

ሕዝቡ በጠላት ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው፥ አሁን ላይ ጠላትን ለመቅበር የሚያስችል የሕዝብ ንቅናቄ መፈጠሩን አንስተዋል።

የልማት ሥራም ሆነ ውጊያ ውጤታማ የሚሆነው መሪ ከፊት ሲገኝ ነው ያሉት አስተዳዳሪው፥ ጦርነት ከፊት ሆኜ የምመራው ለሕዝብና ለራሴም ክብር ነው ብለዋል።

የዞኑ መሪዎችም ጠላትን መፋለም የሚያስችል ስምሪት ማድረጋቸውን ነው ያስታወቁት።

ለህልውና ዘመቻው በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.