Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን የሩዝ ምርት መሰብሰብ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን ከ2 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ እየለማ የነበረ የሩዝ ምርት መሰብሰብ ተጀመረ።

ምርቱ በአርሶ አደሮች፣ በማህበር በተደራጁ ወጣቶችና በባለሃብቶች የለማ ሲሆን ÷የዞኑ አመራሮች በተገኙበት በሸቤ ወረዳ መሰብሰብ ተጀምሯል።

የዞኑ ምክትል አስተዳደር አቶ የሱፍ ሻሮ፥ ዘመናዊ የግብርና ዘዴን ተግባራዊ ማድረግ ከተቻለ በምግብ እህል እራስን በመቻል ከተረጂነት መላቀቅ ይቻላል ነው ያሉት።

በዞኑ በሩዝ እየለማ ካለው መሬት ላይ 84 ሺህ ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን የጅማ ዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኤሊያስ ተናግረዋል።

በሙክታር ጠሃ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.