Fana: At a Speed of Life!

የፈረንሳይ ወታደሮች በማሊ 30 እስላማዊ ታጣቂዎችን ገደሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፈረንሳይ ወታደሮች ከ30 በላይ አክራሪ ታጣቂዎች መግደላቸውን የፈረንሳይ ጦር ሃይል አስታወቀ።

ታጣቂዎቹ ጎሩማ እና ሊፕታኮ በተባሉ አካባቢዎች በተካሄዱ ሶስት ዘመቻዎች መገደላቸውንም ነው ጦሩ ያስታወቀው።

ዘመቻው በአነስተኛ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን)፣ በጦር አውሮፕላን እና በሁለት ሄሊኮፕተሮች የታገዘ ነበር ተብሏል።

ዘመቻው ከአልቃይዳ እና አይ ኤስ ጋር ግንኙነት አላቸው በተባሉ ታጣቂዎች ላይ ማሊ ከሞሪታኒያ በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ የተካሄደ ነው።

ፈረንሳይ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖችን ለመዋጋት 4 ሺህ 500 ወታደሮቿን አሰማርታለች።

ከዚህ ባለፈም በአካባቢው ያላትን የጦር ቁጥር ለማሳደግ ተጨማሪ 600 ወታደሮች ለማሰማራት እቅድ እንዳላት አስታውቃለች።

ወታደሮቹ በብዛት በማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር ይሰማራሉም ነው የተባለው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማሊ ውስጥ 13 ሺህ ጠንካራ የሰላም አስከባሪ ሀይል እንዳለው ይነገራል።

በሳህል ቀጠና ተመድን ጨምሮ ፈረንሳይ እና አሜሪካ ሰላም ለማስፈን በርካታ ገንዘብ ቢያፈሱም የታሰበውን ያክል ውጤት አላመጣም።

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.