Fana: At a Speed of Life!

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ3 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2013 የትምህርት ዘመን በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 559 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።

ከዚህ ውስጥ 3 ሺህ 431 በመጀመሪያ ዲግሪ፥ ቀሪዎቹ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል ከተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ ጎረቤት ኀገራት የመጡ 22 ተማሪዎች ይገኙበታል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲፕሬዚደንት ዶክተር ኡባህ አደም÷ ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመበት 1999 ዓ.ም. ጀምሮ ከመማር ማስተማር በተጨማሪ የማህበረሰብ ችግር ፈቺ የሆኑ ምርምሮች ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

አሁን ላይም በኀገር በቀል እውቀቶች ላይ ያተኮሩ 128 የምርምር ስራዎችን እያካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማሣለጥ በ65 ሚሊየን ብር የቤተ ሙከራና የምርምር ማዕከል ግንባታ እያካሄደ መሆኑን አመላክተዋል።

በምረቃ ስነ ስርአት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ስርአት ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትርና የዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዛዲግ አብርሃ እንደተናገሩት÷ አሁን ላይ ሃገሬ ለእኔ ምን አደረገችልኝ በሚል የሚጠየቅበት ሳይሆን÷ እኔ ለሃገሬ ምን ላድርግ ተብሎ የሚጠይቅበት ሊሆን ይገባል ብሏል፡፡

የሃገር ህልውና ለማስተባበርና አሸባሪውን የህወሓት በድን ለመደምስስና የሃገር ህልውና ሉአላዊነት ለማዳን የተጀመረውን ጥረት በመቀላቀል የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ልታበረከቱ ይገባል ብለዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በበኩላቸው÷ አገራችን ከውስጥም ከውጪም ፈተና የተደቀነባት ጊዜ በመሆኑ አካባቢን በንቃት በመጠበቅ የሠርጎ ገቦችንና የፀጉረ ልውጥ እንቅስቃሴን በንቃት መጠበቅና ለአገር መከላከያ ሠራዊት ደጀን መሆን እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

በተሾመ ኃይሉ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.