Fana: At a Speed of Life!

ሲ ኤን ኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢትዮጵያን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃ እያወጣ መሆኑ ተጋለጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲ ኤን ኤን የተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢትዮጵያን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃ እያወጣ እንደሆነ ተጋለጠ።

ጣቢያው ኢትዮጵያን በተመለከተ ተደጋጋሚ ዘገባዎችን እየሰራ ቢገኝም፥ የሚሰራቸው ዘገባዎች በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረቱ ሐሰተኛ፣ የተዛቡና ሚዛናዊነት የጎደላቸው ናቸው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

የቴክኖሎጂ አማካሪና ስትራቴጂስት የሆነው የቴክቶክ ዋና አዘጋጅ ሰሎሞን ካሳ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ እንዳደረገው፥ ሲ ኤን ኤን በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት በሰራው አንድ ዘገባ ላይ ሀሰተኛ ምስል መጠቀሙን አጋልጧል።

“ምንም ነገር ተሸሽጎ ለዘላለም አይቆይም” በሚለው መርሁ የሚታወቀው ኡጋንዳዊው የምርመራ ጋዜጠኛው ዳኒኤል ሉታያ በበኩሉ ወደ ኢትዮጵያ ከማቅናቱ በፊት የሲ ኤን ኤን ዘገባዎችን ተመልክቶ እንደነበር ገልጿል።

በዘገባው መሰረት ወደለየለት የጦር ቀጠና እየገባ እንደሆነ ተሰምቶት እንደነበር በትዊተር ገጹ አስነብቧል።

ነገር ግን ኢትዮጵያ ሲደርስ ያጋጠመው የሲ ኤን ኤን ዘገባ ከፈጠረበት ምስል ተቃራኒ እንደሆነም ጋዜጠኛው አስታውቋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.