Fana: At a Speed of Life!

ሀረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን 846 ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡
ኮሌጁ ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ከማፍራት አንፃር እያከናወነ ባለው ተግባር የክልሉ መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገልጸዋል፡፡
እንደ ሀገር ያጋጠመንን የህልውና አደጋ በማያዳግም ሁኔታ መቀልበስ የሁሉም ዜጋ ርብርብ ወሳኝ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ አንስተዋል፡፡
ተመራቂዎችም ከሀገር መከላከያ ፣ የፌደራልና የክልሎች የጸጥታ ኃይል አባላት ጎን በመሰለፍ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ኢብሳ ሙሳ በበኩላቸው÷ ተመራቂዎች የቀሰሙትን እውቀት ተግባር ላይ በማዋል በተለይም የማህበረሰቡን የጤና ችግር እንዲቀርፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በእለቱ የጤና ሳይንስ ኮሌጁ በ9 የዲግሪ እና በ8 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መርሃግብሮች ያሰለጠናቸውን 846 ተማሪዎችን የሥመረቀ ሲሆን÷ ከተመራቂዎቹ መካከልም 49 በመቶ ሴቶች መሆናቸውን ከሃረር ጤና ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡
ከተመራቂዎቹ መካከልም 82 ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል የተሰጡ ናቸው ተብሏል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.