Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ለህልዉና ዘመቻዉ ከ 121 ሚልየን ብር በላይ ግምት ያለው የጥሬ ገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረጉ።
በሁለተኛው ዙር የህልውና ዘመቻ የድጋፍ ማሰባሰብ ሂደት 69 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቡን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የህልውና ዘመቻው የሎጀስቲክ ስራዎች አስተባባሪ አቶ ባዩ አቡሃይ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪ 52 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ደረቅ የስንቅ ራሽንም ተዘጋጅቷል ነው ያሉት፡፡
የተሰበሰበው ደረቅ ምግብ÷ ግልፅ አደረጃጀት በመዘርጋት በግንባር ላይ ለሚገኘው ሃይል እንዲደርስ እየተደረገ መሆኑንም ምክትል ከንቲባዉ ገልፀዋል።
በማራኪ ክፍለከተማ የህዳሴ ቀበሌ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሻምበል አዲስ ብዙ በበኩላቸው÷ የህዳሴ ቀበሌ ነዋሪዎች በየቀጠናው ስንቅ እያዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የስንቅ ዝግጅቱ ተጠናክሮ አንደሚቀጥልም ስራ አስኪያጅዋ መናገራቸዉን ከጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.