Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ህውሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል በነገው እለት አሸባሪዎቹ ህውሓት እና ሸኔን የሚያወግዝ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊትንና ሌሎች የፀጥታ ሃይሎችን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ገለጹ።
ህውሓትና ሸኔ እያደረሱት ያለውን ጉዳት የሚያወግዝ እንዲሁም ሀገርን ለማዳን የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙት የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የክልል የጸጥታ ሀይሎች የድጋፍ ሰልፍ ይካሄዳል ብለዋል ኃላፊው።
በክልሉ በገጠርና ከተማ የሚኖረውን ህዝብ በማሳተፍ የሚካሄደው ሰልፉ÷ በሀረር ከተማ በሚገኘው ኢማም አህመድ ስታድየም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ነው የገለጹት፡፡
ህዝባዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ እና የተሳካ እንዲሆን አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉን ጠቁመው÷ መላው የክልሉ ነዋሪ በነቂስ በመውጣት በሰልፉ ላይ እንዲሳተፉም ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የክልሉ ህዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ ድጋፉን በማጠናከር ሀገር በማዳኑ ተግባር የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት የጠየቁት የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ÷ ወጣቶችም የሀገር መከላከያን በመቀላቀልም ሀገርን መታደግ አለባቸው ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.