Fana: At a Speed of Life!

አባቶቻችን አልተንበረከኩም፤ እኛም አንንበረከክም – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መላው የአዲስ አበባ ነዋሪ ዓለም በኢትዮጵያ ላይ ለሚቃጣው ፀረ ሉዓላዊነት አካሄድ በአንድነት ማውገዝ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሰፈሩት÷ አዲስአበባ ተከባለች ለሚሉ ሀይሎች እና ሚዲያዎቻቸው÷ አዎ አዲስ አበባ ዙሪያዋን የተከበበችዉ አመታትን ባስቆጠሩት ጥብቅ የእንጦጦ ፣ የየካና የጉለሌ ዉብ ደኖችና እንዲሁም አብረዋት እያደጉ ያሉ እህልና ዉሃ በሚያቀርቡላት እህት ከተሞቿ ነዉ ብለዋል፡፡
በነገው ዕለት በመስቀል ዐደባባይ በሚካሄደው ሰልፍ በመገኘትም÷ ኢትዮጵያ በክብሯ ላይ ለሚቃጣ እርምጃ እንደማትንበረከክ እንዲሁም ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የማይበገር ደጀንነታችንን ልናሳይ ይገባል ብለዋል፡፡
መቼም ኢትዮጵያን የማንክዳት፤ ለባእዳን የቀን ቅዠት አሳልፈን የማንሰጣት የጀግኖች ልጆች መሆናችንን÷ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ክብር በአንድነት ዘብ መቆማችንን በድጋሚ እናሳዉቅ የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.