Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን እቃወማለሁ – ደቡብ ሱዳን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚደረግ የውጭ ጣልቃገብነትን እንደማትደግፍ በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ሞርጋን ተናገሩ።
በዓለም ታሪክ ውስጥ ቀደምት ሀገር መሆኗን የጠቆሙት አምባሳደሩ÷ ችግሮቿንም በራሷ አቅም መፍታት የሚያስችል ልምድ ያካበተች ሀገር ናት ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍ ኔሽን እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራች እንደመሆኗ ችግሮቿን እንዴት መፍታት እንዳለባት የካበተ ልምድ ያዳበረች ሀገር መሆኗን ገልጸዋል፡፡
ደቡብ ሱዳንም ኢትዮጵያ ችግሮቿን በራሷ አቅም መፍታት እንደምትችል ጽኑ እምነት እንዳላት ጠቁመው÷ ይህ በመሆኑም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚደረግ የውጭ ጣልቃግብነትን ፈጽሞ አንደግፍም ብለዋል።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልቫኪር ማያርዲት በቅርቡ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን በማስታወስ “ኢትዮጵያ ሁሌም ከደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ጎን ናት፤ ለእኛም ሁለተኛ አገራችን ናት” ብለዋል አምባሳደሩ፡፡
ኢትዮጵያ ቤታችን እንደሆነች ይሰማናል፤ በቤታችን ችግር ሲፈጠር ደግሞ ደስታችን ይርቃል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ረጅም ርቀት በጋራ ተጉዘዋል ያሉት አምባሳደሩ “በሁለት አገር የምንኖር አንድ ሕዝብ ነን” ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተያዘች ነጻ አፍሪካዊት አገር መሆኗን ያስታወሱት አምባሳደሩ÷ በዚህም የሁሉም አፍሪካዊያን ዐይን ኢትዮጵያ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ትምህርት በሚሆን መልኩ የተሳካ ሠላማዊ ምርጫ ማካሄዷንም አምባሳደር ጀምስ ሞርጋን ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደት አይተኬ ሚና እንዳላት ጠቅሰው÷ ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ ሠላም ለቀጣናውም ፋይዳው የጎላ መሆኑን አውስተዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.