Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ተግባራዊ የሚደረጉ ክልከላዎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መምሪያ የሚተላለፉ መመሪያወች እንደተጠበቁ ሆነው÷ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ የሚደረጉየክልከላ መመሪያዎች አውጥቷል፡፡
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
1.በክልሉ ውስጥ ባሉ አካባቢወች ማንኛውም ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ከቀኑ 12፡00 ሰዓት በኋላ እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ ነው፤
2.ማንኛውም የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ባለ ሶስት እግርን ጨምሮ ከምሽቱ 2፡00 በጓላ ማንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
3.የምርት ዕንቅስቃሴ እንዳይስተጓጎል የጭነት መኪኖች በየኬላው ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገባቸው እንዲንቀሳቀሱ የፈቀድላቸው ሆኖ ከረዳቱና ካሽከርካሪው ውጪ መጫን የተከለከለ ነው፤
4.ከፀጥታ አካላት ውጪ ማንኛውም እግረኛ በክልሉ ውስጥ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
5.ከጤና ተቋማት፣ከነዳጅ ማደያዎች፤ከፖሊስ ጣብያ ውጪ ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ተቋም ከምሽቱ 3፡00 በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም፤
6.ማንኛውም ባለ ሁለት እግር ተሸከርካሪና አሽከርካሪ የመንግስትን ጨምሮ ከቀን 29/2/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 3/3/2014 ዓ.ም ድረስ በአቅራብያቸው ባለው የፖሊስ ተቋም ቀርበው መመዝገብ አለባቸው፤
የደቡብ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት
ጥቅምት 27/2014ዓ.ም
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.