Fana: At a Speed of Life!

የአድዋ ልጆች መሆናችንን እረስተው በአጎዋ ሊያስፈራሩን ይሞክራሉ-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ ምዕራባውያን ሃገሮች የአድዋ ልጆች መሆናችንን እረስተው በአጉዋ ሊያስፈራሩን ይሞክራሉ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
ከንቲባዋ በመስቀን አደባባይ በተካሄደው አሸባሪዎቹን ህወሓት እና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ ላይ ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ በመስቀን አደባባይ በተካሄደው አሸባሪዎቹን ህወሓት እና ሸኔን የሚያወግዘው ሰልፍ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፥አሸባሪዎቹን በመደምሰስ የሃገራችንን ሉዓላዊነት ለማስከበር የዛሬው ትውልድ ቆራጥ ነው ብለዋል፡፡

የዲሞክራሲ ደቀ መዝሙር ነን የሚሉ ምዕራባያን የኛን ዲሞክራሲ ሲጋፉ ተስተውሏል ያሉት ከንቲባዋ ምእራባውያኑ አለም በኢትዮጵያ ላይ የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖረው የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሚዲያዎቻቸውንም አዝምተውብናል ብለዋል ወይዘሮ አዳነች ፡፡

ተላላኪዎቹን ህወሓትና ሸኔ ሃገር የማፍረስ ተልዕኳቸውን በመመከት ሉዓላዊነታችችን ለማስከበር ሁሉም የህልውና ዘመቻውን እንዲቀላቀልም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ነፃነታችንን ሊነጥቀን የመጣን ሃይል የምንሸከምበት ትከሻ የለንም ያሉት ከንቲባዋ በሃገራችን ከመጡብን የምሳሳለት ሕይዋት ሃብት እና ንብረት ሊኖረን አይገባም ብለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.