Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ከአለም የምግብ መርሀ ግብር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢሲ)የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ከአለም የምግብ መርሀ ግብር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

አሸባሪ ቡድኑ በወረራ በያዛቸው የአማራ ክልል አካባዎች ንፁሀንን ከመግደል እስከ ማፈናቀል የደረሱ ግፎችን እየፈፀመ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ አንስተዋል።

የክልሉ መንግስት በአሸባሪ ቡድን ምክንያት ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ለመርዳት ጥረት እያደረገ ቢሆንም ባለው የአቅም ውስንነት ምክንያት ችግሩን ማቃለል አለመቻሉን ገልፀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ ተቋማት እስካሁን ችግሩን ለማቃለል ላደረጉት ርብርብ ምስጋና ያቀረቡት ዶክተር ይልቃል አሁንም በአሸባሪ ቡድኑ ህወሓት ምክንያት ችግር ላይ የወደቁ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ አሁንም አፋጣኝ ድጋፍ በማድረግ ችግሩን ለማቃለል እገዛ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአሸባሪ ቡድኑ ወረራ ምክንያት 7 ሚሊዮን የሚሆኑ የክልሉ ነዋሪወች አደጋ ላይ መውደቃቸውንና ከዚህ ውስጥ 6 ሚሊዮን የሚሆኑት አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው ተብሏል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.