Fana: At a Speed of Life!

በአምቦ አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የምዕራብ ሸዋ ህዝብ አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን በማውገዝና መከላከያ ሰራዊትን በመደገፍ በአምቦ ከተማ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ፡፡

በሰልፉ አምቦ ከተማን ጨምሮ በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

ሰልፈኞቹ የሸብርተኞቹን ህወሃትና ሸኔ ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማና ህልም ለማምከን ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

‘የአሸባሪዎቹን ሀገር የማጥፋት የጭካኔ ድርጊቶችን አንድ ሆነን እንመክታለን!፤ ኢትዮጵያ ለጠላት ተንበርክካ አታውቅም፤ ሸኔና ወያኔ የኦሮሞ ጠላቶች ናቸው፤ የኦሮሞ ህዝብ ለወያኔ እጁን አይሰጥም፤ ወያኔና ሸኔ የቀሬና ቄሮ ዋና ጠላቶች ናቸው’ የሚሉ መፈክሮችን በማስተጋባት ሰልፈኞቹ ህወሃትና ሸኔን አውግዘዋል፡፡

‘ክብር ለመከላከያ ሰራዊታችን፤ መከላከያ ሰራዊት ሃይላችን ነው፤ መከላከያ ሰራዊት አጥራችን ነው፣ ይጠብቀናል እናከብረዋለን፤ አካባቢዬን እጠብቃለሁ፤ አገሬን ለማዳን እዘምታለዉ፤’ የሚሉና መሰል መፈክሮችንም በማስተጋባት ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

”የህወሃት ተልዕኮን የሚያስፈፅሙ በየአካባቢው ተሰግስገው የሚገኙ ባንዳዎችን በማጋለጥ የበኩላችንን እንወጣለን” ሲሉም በጋራ ቃላቸው ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.