Fana: At a Speed of Life!

በውሸት ፕሮፖጋንዳ ስነ ልቦናዊ ሽንፈትን የምንቀበልበት ሁኔታ አይኖርም -የስልጤ ዞን እና የወራቤ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድንና ቅጥረኞቹ በተለያዩ መንገዶች የከፈቱትን ሀገርን የማፍረስ ተግባር እንደሚያወግዙ የሰልጤ ዞን እና የወራቤ ከተማ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ገለፁ፡፡

በሰልፉ ላይ በዞኑ ዉሰጥ ከሚገኙ ወረዳዎች እና ወራቤ ከተማ አስተዳዳር የተውጣጡ ነዋሪዎች ተሳተፈዋል፡፡

መንግስት ጁንታዉን ለመደመስሰ የሚወሰደዉን ማንኛዉንም እርምጃዎችን እንደሚደግፉ በመናገር የሀገራችን ዘብና መከታ በሆነው መከላከያ ሀይላችን ጎን በመቆም አጋርነታችንን እናሳያለን ብለዋል፡፡

የሃገሪቱን ህልውና ለማስጠበቅ እና በሽብርተኛው ህወሃት ቡድን አማካኝነት በውስጥና በውጭ ኃይሎች የተቃጣውን የጥቃት ዘመቻ ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ለመመከት መዘጋጀታችዉንም ተናገረዋል፡፡

የዞኑ ነዋሪዎች በአንድ እጃችን ጁንታዉን እየወጋን በሌላዉ እጃችን ልማትን እየሰራን ከፍ ብለን በመዉጣት የጠላትን አንገት እናስደፋለን፣ለዚህም ደግሞ አንድነታችንን ከምንጊዜዉም በላይ ማጠናከር ይኖረብናል ብለዋል፡፡

ለሀሰተኛ መረጃዎች ጆሮ ሳይሰጡ ከመንግስት ጎን በመሆን የተኛዉንም ድጋፍ ለማድረግ ቁርጥኛ መሆናቸዉን አንስተዋል፡፡

በሰልፉ ላይ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ እየተሰበሰበ ሲሆን የደም ልገሳ ፕሮግራምም ተከናውኗል፡፡

በኦሊያድ በዳኔ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.