Fana: At a Speed of Life!

በሀገር ሉዓላዊነት ላይ ምንም ዓይነት ድርድር የለንም-የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርባ ምንጭ ከተማ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ የአሸባሪዎችን ህወሓት እና ሸኔን ሴራ የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ እንዲሁም ደም የመለገስ መርሃ ግብር በዛሬው እለት ተከናውኗል ።

ከጋሞ ዞን ከሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የጋሞ ሰላም አባቶች ፣የኃይማኖት መሪዎች እና በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰልፉ ላይ ተሳትፈዋል ።

” የድላችን ሚስጥሮች ፍትህ ፤ሀቅ እና እውነት ናቸው፤ በሀገር ሉዓላዊነት ላይ ምንም ዓይነት ድርድር የለንም፣በየትኛውም ሁኔታ እስከ ግንባር ድረስ ለመሄድ ተዘጋጅተናል፣የአባቶቻችን ታሪክ የመጠበቅ አደራ አለብን የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ሰልፈኞቹ አሰምተዋል፡፡

የሰልፉ ተሳታፊዎች በተባበረ ክንድ የጁንታውን ህልም ከንቱ በማድረግ በግንባርም በመዝመት የበኩላቸውን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብራሃኑ ዘውዴ ህወሓት በስልጣን በነበረበት ጊዜ ለራሱ አገዛዝ እንዲመች ህዝብን በማከፋፈል መተማመን እንዳይኖር ሲያደርግ ነበር አስታውሰው የኢትዮጵያ ህዝብ በአሽከር ተላላኪ አይመራም፤አሁን የሚታየው ፈተና ባለፈው 27 ዓመታትን የተሰራ የሴራ ውጤት ነው ብለዋል።

ከሰልፉ በተጨማሪ ለጀግናዉ መከላከያ ሰራዊት ደም የመለገስ መርሃ ግብርም ተከናውኗል፡፡

በማቴዎስ ፈለቀ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.